Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 08, 2025 .

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት መሰረት መስከረም 29 ቀን 2018 ዓም የንግድ ትግበራዋን ልትጀምር ነው

▶️ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት መሰረት መስከረም 29 ቀን 2018 ዓም የንግድ ትግበራዋን ልትጀምር ነው

▶️ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት መሰረት መስከረም 29 ቀን 2018 ዓም የተለያዩ ምርቶችን በመላክ የንግድ ትግበራዋን እንደምትጀምር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

▶️ በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የስራ ሀላፊዎች እንደሚታደሙ ተገልጿል።

▶️ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ያስሚን ወሀብረቢ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ግብይትን ለማስጀመር በርካታ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይተዋል።

▶️ ኢትዮጵያ ስምምነቱን በመፈረም ቁርጠኝነቷን ያሳየች መሆኑን ገልጸው፤በአሁኑ ወቅት የግብይት ስርዓቱን ለማስጀመር ዝግጅት የተጠናቀቀ መሆኑን ገልፀዋል።

▶️ ነፃ የንግድ ግብይት መጀመሩ በኢትዮጵያ በወጪ ንግድ ዘርፍ እየታየ ያለውን እድገት ለማስቀጠል ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸው፤የሀገር ውስጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለማሳደግ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል።

▶️ ግብይቱ መጀመሩ ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኢኮኖሚ ለማስተሳሰር የምታደርገውን ጥረት የሚያፋጥን መሆኑን ገልፀዋል።

▶️ በዚህም ግብይቱ በአፍሪካ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የሚደረግ ሲሆን መስከረም 29 ቀን 2018 ዓም በሚካሔደው የጭነት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ምርቶችን የመላክ ስራው እንደሚጀመር መናገራቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

▶️ በዚህም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ሥጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በየብስ ትራንፖርት ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ አፍሪካ እንደሚላክ አብራርተዋል፡፡

▶️ ስምምነቱ ለነጋዴዎች፣ለወጣቶች፣ለስራ ፈጣሪዎችና ሴቶች ተጨማሪ የስራ እድል ይዞ ከመምጣቱ ባሻገር ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እንደሚረዳም ነው የጠቀሱት።
(AMN)

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia