Oct 08, 2025 .
በተፈጥሮ ጋዝ የማይሰሩ ከባድ መኪናዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት አይፈቀድም፡- ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር!

እንደሀገር የተፈጥሮ ጋዝ ማምረት መጀመራችንን ተከትሎ የትራንስፖርት ዘርፉን በተፈጥሮ ጋዝ ወደሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ለማሸጋገር አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ ይገኛል።
በቀጣይም በተፈጥሮ ጋዝ የሚንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎች ብቻ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ እና እንዲሰሩ ይፈቀድላቸዋል።
በዚህም መሠረት በተፈጥሮ ጋዝ የማይሰሩ ከባድ መኪናዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት እንደማይፈቀድ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት በአክብሮት እናሳውቃለን።
በመሆኑም አስመጪዎች ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የማስገባት ፍቃድ ሳታገኙ ምንም አይነት ከባድ መኪና ግዢ እንዳትፈጽሙ እና ይህ ማስታወቂያ ከወጣ በኋላ የሚደረጉ ግዥዎች የማስገቢያ ፈቃድ የማይሰጣቸው በመሆኑ በተፈጥሮ ጋዝ በሚንቀሳቀሱ ከባድ መኪናዎች ብቻ የተገደቡ እንዲሆኑ እንገልጻለን።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር!

