Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 10, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በተለያዩ የቢዝነስ መሥኮች ለሚያሠለጥኑ አሠልጣኞች  ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቀቀ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በተለያዩ የቢዝነስ መሥኮች ለሚያሠለጥኑ አሠልጣኞች  ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቀቀ።

ስልጠናው ምክር ቤቱ ከSNV – LIWAY ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን የቢዝነስ ተቋማትን አቅም ለመገንባት ያለመ ነው።

ስልጠናው በሥልጠና ዝግጅትና አሰጣጥ፣ በዲጂታል ማርኬቲንግና ኢ- ኮሜርስ፣ በማሥታወቂያ፣ ብራንዲንግ እንዲሁም በሌሎች መሥኮች ላይ ያተኮረ ነው።

በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ፀደቀ ድጋፌ አሠልጣኞች ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ለሠልጣኞች በአግባቡ በመሥጠት በቢዝነስ ተቋማት ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ለሰልጣኝ አሰልጣኞችም የስልጠና ማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት ከምክር ቤቱ ተሰጥቷቸዋል፡፡

SNV የተሠኘው ዓለም አቀፍ ተቋምም በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ፕሮጀክቶች ላይ እየሠራ ያለ ተቋም ነው።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከሚሠጣቸው አገልግሎቶች አንዱ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሥጠት መሆኑ ይታወቃል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia