Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 22, 2025 .

በፈረንጆቹ መጋቢት 2026 በሚካሄደው የዓለም የንግድ ድርጅት 14ኛ የሚኒስትሮች ጉባዔ ወቅት ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ መሆኗን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ገለጹ።

▶️ የዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት ጉዳይ

▶️ ኢትዮጵያ የአባልነት ድርድሩን በካሜሩን ያውንዴ በፈረንጆቹ መጋቢት 2026 በሚካሄደው የዓለም የንግድ ድርጅት 14ኛ የሚኒስትሮች ጉባዔ ወቅት ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ መሆኗን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ገለጹ።

▶️ ገዥው ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) በዓለም የንግድ ድርጅትና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች የአሜሪካ ረዳት የንግድ ተወካይ ኒል ቤክ ጋር የኢትዮጵያን የዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት ድርድርን በተመለከተ ተወያይተዋል።

▶️ በውይይታቸውም የኢትዮጵያን የዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት አስመልክቶ የተካሄደውን የስድስተኛ የስራ ቡድን ስብሰባ ውጤት እና ከስብሰባው በኋላ የተከናወኑ ቁልፍ ማሻሻያዎችን አብራርተዋል።

▶️ ኢትዮጵያ ድርጅቱን ለመቀላቀል አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችን ለማሟላት ያላትንም ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

▶️ ኢትዮጵያ ከአባል ሀገራትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የምታገኘውን ከፍተኛ ድጋፍ ጠቅሰው፤ አሜሪካም በዚህ ረገድ የተጠናከረ ድጋፍ እንድታደርግ ነው የጠየቁት።

▶️ በዓለም የንግድ ድርጅት እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች የአሜሪካ ረዳት የንግድ ተወካይ ኒል ቤክ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እየሰራችው ያለውን ስራ አድንቀው አሜሪካ ተገቢውን ተሳትፎ እንደምታደርግ አስታውቀዋል።

▶️ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ማሟላት ያለባትን መስፈርት በግልፀኝነት ለማሳወቅም እንደሚሰሩም ተናግረዋል።(ENA)

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia