Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 07, 2025 .

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ ከክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ።

ለፈጣን_ኢኮኖሚ_ዕድገት ተወዳዳሪ የሆነ የግሉን ዘርፍ መፈጠር ያስፈልጋል:- አቶ ዘሪሁን ቃሚሶ (ፕሬዝዳንት)

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ ከክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በቅንጅት የተሰሩ ሥራዎችን በመገምገም በቀጣይ ጊዜያት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደ።

የክልሉ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ዘሪሁን ቃሚሶ በመክፈቻ ንግግራቸው እስካሁን ከንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በጋራ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይም ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

 

አክለው ሀገራችን በቅርቡ የተጀመረው AfCFTA የንግዱ ዘርፍ ሰፊ የገበያ እድል እንዲያገኝ መንገድ የከፈተ እና ተወዳዳሪነት እንደዚሁ ይጨምራል ብለዋል: አያይዘውም በቅርቡ የወጣ የገቢ ግብር አዋጅ በተመለከተ እና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ከሚመለከተው አካል ጋር በጋራ በመሆኑ የግንዛቤ መፈጠር መድረክ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

የሲዳማ ክልል የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሰላማዊት መኩሪያ በበኩላቸው የግሉን ዘርፍ ማጠናከር የመንግሥት ትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ገልጸው እስካሁን የተሰራው ስራ በማበረታታት በቀጣይ እየመጣ ያለውን የንግድ ስርዓት ላይ የክልላችን ነጋዴዎች ተወዳዳሪ መሆን እንዲችሉ በቅንጅት መሠራት እንዳለበት ገልጸዋል።

የምክር ቤት ዋና ፀሐፊ አቶ ደመቀ ደፋሮ እንደ ጽ/ቤት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በማቅረብ በቀጣይ ከክልሉ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በጋራ በምንሰራቸው ጉዳዮች ላይ ለውይይት የሚሆን ጽሑፍ በማቅረብ ሰፊ ውይይት በማድረግ የጋራ አቋም በመያዝ ተጠናቋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia