Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 07, 2025 .

የአዲስ ቻምበር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ከአቻው የአርባ ምንጭ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የአዲስ ቻምበር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ከአርባ ምንጭ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር አቻው ጋር አብሮ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙርያ ውጤታማ ውይይት አካሄደ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ጠንካራ ከሚባሉ ንግድ ምክር ቤቶች አንዱ የሆነው የአርባ ምንጭ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቦርድ አመራሮች በአዲስ ቻምበር ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የስራ ጉብኝት እንዲሁም በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙርያ ጠቃሚ ውይይት አካሄደዋል፡፡

በውይይታቸው ወቅት የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አዲስ ቻምበር የረጅም አመት የስራ ልምድና ተሞክሮ በከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አማካኝነት ለልኡካ ቡድኑ ገለጻ ተደርጓል፡፡

በውይይታቸው ወቅት የአዲስ ቻምበር ፕረዚደንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ ምክር ቤታቸው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የንግዱ ማህበረሰብ ድምጽ ለመሆን በመስራት ላይ እንደሚገኝ የገለጹ ሲሆን ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ከአነስተኛ የንግድ ተቋማት ጀምሮ  እስከ ትላልቅ ኩባንያዎች ድረስ የሚደርስ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በተለይም የሀገር ውስጥ የቢዝነስ ተቋማትን ተወዳዳሪ ለማድረግ ምክር ቤታቸው ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ በመግለጽ በተለይም በውጭ ሀገራት ከሚገኙ አቻ የንግድ ምክር ቤቶች እና የንግድ ተቋማት ጋር በቅርበት በመስራት ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲያድግ በመስራት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ ምክር ቤታቸው የኩባንያ ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት የሚያስችል ስራዎችን በስፋት በመስራት ላይ እንደሚገኝ አክለው ገልጸዋል፡፡

የአዲስ ቻምበር ዋና ጸሀፊ መሰረት ሞላ ( ዶ/ር) በበኩላቸው አዲስ ቻምበር ምቹ የሆነ የንግድና ኢንቨስትመንት ፖሊሲዎች እንዲቀረጹ፤ ተወዳዳሪ የንግድ አውድ እንዲፈጠር፤ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስሮች እንዲዳብሩ የሚያስችሉ የፖሊሲና አድቮኬሲ ስራዎችን ከአጋር አካላት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕረዚደንት ኢንጂነር ቦጋለ ቤታነህ በበኩላቸው ስለ አዲስ ቻምበር ታሪካዊ አመጣጥና እድገት እንዲሁም ስለ አገልግሎት አሰጣጡ ያገኙት መረጃ ለምክር ቤታቸው ሰፊ ልምድና ተሞክሮን እንዳስገኘላቸው የገለጹ ሲሆን ምክር ቤታቸው ከአዲስ ቻምበር ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

በተለይም የሁለቱ ከተሞች ነጋዴዎችን የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል ስልታዊ አጋርነት እንዲጠናከር ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በሁለቱ ምክር ቤቶች የቦርድ አመራሮች መካከል የተደረገው የልምድ ልውውጥ በቀጣይ አብሮ ለመስራት በሚያስችሉ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጓል፡፡

የሁለቱ ተቋማት መሪዎች ከውይይታቸው በኋላ የአዲስ ቻምበር ዋና መስሪያ ቤት ህንጻን እና የስራ ክፍሎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ (የአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት)

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia