Nov 10, 2025 .
የቀርጫንሼ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አስራኤል ደገፋ Sustainable Times RISE Award 2025 ሽልማትን አሸነፉ!!


የቀርጫንሼ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አስራኤል ደገፋ Sustainable Times RISE Award 2025 ሽልማትን አሸነፉ!!
ይህ ዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጣቸው የቡና አርሶአደሮችን ለማብቃት፣ ሙሉ የክትትል ሰንሰለትን (full traceability) ለማረጋገጥ እንዲሁም የኢትዮጵያን አረብካ ቡና ጥራት ለዓለም ለማካፈል ባለ ጽኑ ቁርጠኝነት መሆኑ ተጠቅሷል ።
የዘላቂ ታይምስ RISE ሽልማቶች በፈጠራና በተፅዕኖ አማካይነት ዘላቂነት ያለው መጻኢ ጊዜን በሚቀርጹ ንግዶች ለሚከናወኑ ሥራዎች የሚሰጥ ክብር ነው። በዶክተር እስራኤል ደገፋ መሪነት፣ ቀርጫንሼ ግሩፕ የተጠያቂነት ዕድገትና ዘላቂ ልህቀት (sustainable excellence) ሞዴል ሆኖ መቀጠሉን አሳይቷል።
ከዚህ በተጨማሪ፣ ዶክተር እስራኤል ደገፋ በአፍሪካ አመራር ሽልማቶች (African Leadership Awards) “የ2025 የአመቱ ሰው” ተብለው የተሰየሙ ሲሆን፣ ይህም በአህጉሪቱ ለዘላቂ እድገት ባደረጉት ለውጥ አምጭ አመራርና ቁርጠኝነት የተሰጠ እውቅና ነው። ምንጭ: Oromia post News

