ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቦርድ አባላትና አመራሮች በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ነዉ።


የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከጂ አይ ዜድ ኤዩ ጋር በመተባበር ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና ከክልሉ ለተዉጣጡ የምክር ቤቱ አመራሮች በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና መርሆዎች ዕድሎችና ሊያጋጥሙ በሚችሉ ተግዳሮቶች እንዲሁም ሊደረጉ በሚገቡ ዝግጁነቶች ዙርያ የግንዛቤ መፍጠርያ በቦንጋ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነዉ።
ስልጠናዉን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ አገራችን ነፃ የንግድ ቀጠናዉን ለመቀላቀል አስፈላጊዉን ዝግጅት ስታደርግ ቆይታ በዚህ ዓመት መጀመርያ ላይ ምርቶቿን ወደ ኬንያ ደቡብ አፍሪካና ሶማሊያ በመላክ መጀመሯን በይፋ ማብሰሯን በማዉሳት የአገራችን የንግዱ ማህበረሰብ ለዚህ እየገባንበት ላለዉ ብርቱ ፉክክር እራሱን ማዘጋጀት አለበት ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ በየደረጃዉ ያሉት የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤቶች የንግዱን ማህበረሰብ የማስገንዘብና የማንቃት ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቦርድ አባልና የሚዛን ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አምሳል ነጋሽ ክልሉ ገና የተመሰረት እንደመሆኑ መጠን በየደረጃዉ ያሉ የንግድ ም/ቤቶች አመራሮች የሚቻላቸዉን ሁሉ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ መሆናቸዉን አስረድተዋል።

