Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 22, 2025 .

የዓለም የጥራት ሳምንት ከህዳር 11-14/2018 ዓ.ም “ጥራት በተለየ እሳቤና ፈጠራ” በሚል መሪ ሀሳብ በሀገራችን በመከበር ላይ ነው።

▶️ ጥራት በተለየ እሳቤ እና ፈጠራ!
የዓለም የጥራት ሳምንት ከህዳር 11-14/2018 ዓ.ም “ጥራት በተለየ እሳቤና ፈጠራ” በሚል መሪ ሀሳብ በሀገራችን በመከበር ላይ ነው። ይህ ሳምንት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሁሉም መስኮች የጥራት አስተሳሰብና አሠራር አስፈላጊነት ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን በተለይም ለምግብ ደህንነት፣ ለሰው ልጅ ጤና እና ለኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይታመናል።

▶️ “ጥራት በተለየ እሳቤና ፈጠራ” የሚለው መሪ ቃል ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ደረጃን ያሟላ ጥራት ለማምጣት አዳዲስ የአስተሳሰብ መንገዶችን (Innovative Thinking) እና የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን (Innovation) መጠቀም ወሳኝ መሆኑን ያመለክታል።

▶️ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ማለት ምግብ ከእርሻ ማሳ እስከ ተጠቃሚው ገበታ የሚጓዝበትን መንገድ በሙሉ (አመራረት፣ ማቀነባበር፣ ማጓጓዝ እና ፍጆታን) በማሻሻል ዘላቂ፣ አስተማማኝና ጤናማ እንዲሆን ማድረግ ነው። ጥራት ደግሞ የዚህ ለውጥ ዋና ምሰሶ ነው።

▶️ ጥራት ለምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ስኬት ወሳኝ ከመሆኑ ባሻገር ለሰው ልጅ ጤና እና ለምግብ ደህንነት (Food Safety) የማይተካ ሚና አለው።

▶️ ጥብቅ የጥራት ደረጃዎችንና የንጽህና አሠራሮችን መከተል ምግብን ከባክቴሪያ፣ ከኬሚካል ብክለትና ከሌሎች ጤና ጠንቆች ነፃ ያደርጋል። ይህ ደግሞ በምግብ ምክንያት የሚመጡ በሽታዎችን በመቀነስ የሕዝብ ጤናን ያሻሽላል።

▶️ የጥራት ደረጃዎች የምርት አያያዝንና ማከማቸትን ስለሚያሻሽሉ ምርቱ ከመበላሸትና ከመጣል ይድናል። ይህም በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት ያለውን የምግብ ብክነት በመቀነስ የሀብት አጠቃቀምን ያሻሽላል።

▶️ የጥራት ቁጥጥር የምግቡን የአመጋገብ ይዘት (Nutrition value) እንደተጠበቀ እንዲቆይ ያረጋግጣል፤ ይህም ዜጎች የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙና የረጅም ጊዜ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ይረዳል።

▶️ የጥራት ደረጃን ማሳደግ የኢትዮጵያን አጠቃላይ የምግብ ስርዓት ከማዘመን ባሻገር ለአገሪቱ ኢኮኖሚ በርካታ ጥቅሞችን ያስገኛል፡፡

▶️ ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን ማሟላት ኢትዮጵያ ለውጪ ገበያ የምትልካቸው የግብርና ምርቶች በዓለም ገበያ ተቀባይነት እንዲያገኙ ስሚያስችል ጥራት ያለው ምርት ለውጭ ገበያ ማቅረብ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ያፋጥናል።

▶️ የጥራት ቁጥጥር ስርአቶችን ማጠናከር የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ብቁ እና አስተማማኝ ምርቶችን እንዲያቀርቡ ያግዛል። ይህም የሸማቾችን እምነት በመጨመርና የንግድ ሥራዎችን በማሳደግ በዘርፉ የስራ ዕድል ይፈጥራል።

▶️ የዓለም የጥራት ሳምንት መከበር የኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽንን እውን ለማድረግ፤ ከባህላዊ አሠራሮች ወደ ፈጠራ እና ዘመናዊ የጥራት ቁጥጥር መሸጋገር ወሳኝ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።
ን/ቀ/ት/ሚ

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia