አዲስ ቻምበር አገልግሎቱን እስከ ወረዳ ያሉ ነጋዴዎች እንዲጠቀሙበት አደረጃጀቱን እያጠናከረ መሆኑን ፕሬዚዳንቷ ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ ተናገሩ፤፤

አዲስ ቻምበር አገልግሎቱን እስከ ወረዳ ያሉ ነጋዴዎች እንዲጠቀሙበት አደረጃጀቱን እያጠናከረ መሆኑን ፕሬዚዳንቷ ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ ተናገሩ፤፤
ፕሬዚዳንቷ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስር የተመረጡ የ10 ወረዳ ተወካዮችን የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡ ፤
ንግድ ምክር ቤቱ መዋቅሩን ለማጠናከር ባደረገው ጥረት የክፍለ ከተማውና የወረዳዎቹ ንግድ ጽ/ቤቶች ላበረከቱት አስተዋጽኦ የእውቅና ሰርቲፊኬት አበርክቷል፡፡
የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት በከተማዋ የሚገኙትን ከ 480 ሺህ በላይ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ህጋዊ ነጋዴዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በርካታ የአደረጃጀት ስራዎች እየሰራ ይገኛል፡ ፤
በከተማዋ የሚገኙት ነጋዴዎች ባሉበት ክፍለ ከተማ እና ወረዳ ራሳቸውን እንዲያደራጁ 11 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አዋቅሮ ወደ ስራ ገብቷል፡ ፤
ከእነዚህ አንዱ የለሚኩራ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ አንዱ ሲሆን በስሩ ያሉት 10 ወረዳ ነጋዴዎችን የሚያስተባብሩ የተመረጡ የነጋዴ ተወካዮች በየአካባቢያቸው የንግዱን ማህበረሰብ መብትና ጥቅም እንዲያስከብሩ የአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡ ፤

የአዲስ ቻምበር የለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ ያሉ የንግድ ጽ/ቤቶች ላበረከቱት አስተዋጽኦ የምስጋና እና የእውቅና የመስጠት መርሀ ግብር ተካሂዷል፡ ፤
በመርሀግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት የክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ነጋዴው ጥቅሙና መብቱን እንዲያውቅ በአዲስ ቻምበር ጥላ ስር እንዲደራጅ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡ ፤
ክፍለ ከተማው ለቅርንጫፉ ቢሮ ከመስጠት ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ መዋቅሩን እንዲዘረጋ ሚናው ጎላ ነው ሲሉ አክለዋል፤ ፤ በመሆኑም ለክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ሀላፊና ለ10 ወረዳ ጽ/ቤት ሀላፊዎች የእውቅና እና የምስጋና ሰርቲፊኬት ሰጥተዋል፡
የክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ቢሰጠኝ በበኩላቸው የተደራጀ ህጋዊ ነጋዴ መኖር ለኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ መሆኑን ተናግረው ንግድ ምክር ቤቱ ለሚያደርገው ጥረት ከጎኑ እንደሚሆኑ አስረድተዋል፡ ፤
የአዲስ ቻምበር ዋና ፀሀፊ ዶ/ር መሰረት ሞላ በበኩላቸው ንግድ ምክር ቤቱ አድቮኬሲና የንግድ ድጋፍ አገልግሎቶችን ነጋዴው ባለበት ለማቅረብ በርካታ እንቅስቃሴዎች እተደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል፡ ፤
የአዲስ ቻምበር የለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ሰብሳቢ አቶ መሀመድ ሙስጠፋ እንደተናገሩት በየወረዳ ያሉ የነጋዴ ተወካዮች የንግዱን ማህበረሰብ ችግር ነቅሰው በማውጣት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርበው መፍታት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡ ፤
በመርሀግብሩ ላይ ከ ሁሉም ወረዳ የተውጣጡ ከ 50 በላይ የነጋዴ ተወካዮችና ንግድ ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተገኝተዋል::(አዲስ ቻምበር)

