Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Dec 09, 2025 .

የብሔራዊ ጥራት መሰረተ ልማት ፕሮጀክት (National Quality Infrastructure Project) የመዝጊያ መርሃ ግብር አካሄደ ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለስምንት ዓመታት የዘለቀው የብሔራዊ ጥራት መሰረተ ልማት ፕሮጀክት (National Quality Infrastructure Project) የመዝጊያ መርሃ ግብር አካሄደ ።

በዚሁ መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያን የንግድ ዘርፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እና የቴክኒክ ንግድ እንቅፋቶችን ለመቀነስ ወሳኝ አስተዋጽኦ ማድረጉን  ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጭነት፣ በሀገሪቱ ሰፊ የንግድና ኢንቨስትመት ዘርፍ እንቅስቃሴ ውስጥ የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት እና የግሉ ዘርፍ ሚና ወሳኝነት እንዲኖረው በማስቻል፣ የኢኮኖሚ ምህዳርን ለማሻሻል ያለመ መሆኑን ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አባል መሆኗን አስታውሰው፣ የሀገሪቱን የንግድና የኢንቨስትመንት አቅም ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።

የብሔራዊ ጥራት መሰረተ ልማት ፕሮጀክት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የምርቶች ጥራትና ደህንነት ሥርዓት ለመዘርጋት መሰረት በመጣል፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና እንቅፋቶችን በማስወገድ የኢትዮጵያ ምርቶች ወደ ውጭ ገበያዎች ያላቸውን ተደራሽነት ለማሳደግ ትልቅ እገዛ አድርጓል ብለዋል።

እንደሚኒስትሩ ገለፃ ፕሮጀክቱ የብሔራዊ ጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት (የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት፣ የሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት) ቴክኒካዊ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ረድቷል ሲሉ ተናግረዋል::

ሚኒስትሩ የመዝጊያውን መርሃ ግብር ሲያጠቃልሉ፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  የተቋማትን አቅም የማጎልበት ሥራ ቀጣይነት እንዲኖረው ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

የጥራት መሰረተ ልማትና ማረጋገጫ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን በበኩላቸው ኢትዮጵያን የሚመጥን የጥራት መሰረተ ልማት ተገንብቷል ብለዋል::
ከስምንት ዓመት በፊት ተጀምሮ ዛሬ ፍፃሜው ይፋ የሆነው የብሔራዊ ጥራት መሰረተ ልማት ፕሮጀክት (NQIP) ብዙ ፈተናዎችን አልፎ ኢትዮጵያን የሚመጥን የጥራት መሰረተ ልማት(ተቋም) ሆኖ ተገንብቷል ሲሉ ገልጸዋል::
ሚኒስትር ዴኤታው አቶ እንዳለው መኮንን እንዳብራሩት፣ ፕሮጀክቱ የተጀመረው ከ8 ዓመት በፊት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ “ኢትዮጵያን የሚመጥን ተቋም መገንባት አለብን” በሚል የሰጡት ሀሳብ አመንጭነት ነው።

ፕሮጀክቱ በዋነኛነት በጨርቃጨርቅ፣ በቆዳ እና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፎች ላይ የነበሩ የጥራት መፈተሻ ውስንነቶችን ለመፍታት ያለመ ሲሆን፣ ለዚህም 50 ሚሊዮን ዶላር ተመድቦለት ነው የተጀመረው።

በትግበራ ሂደቱ ወቅት እንደ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና ጦርነት የመሳሰሉ ከባድ ተግዳሮቶች ገጥመውት እንደነበር የገለጹት አቶ እንዳለው ከገጠሙት ችግሮች ተላቆ ለፍጻሜ እንዲበቃ አስተዋፆ ለነበራቸው አካላት በሙሉ ትልቅ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አቶ እንዳለው መኮንን ፕሮጀክቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የሚጠበቁ ሁለት ዋና ዋና ተግባራት እንዳሉ አስቀምጠዋል። ከነዚህ ውስጥ የተፈጠረውን አቅም እና የተተከሉ ዘመናዊ መሣሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር በማስገባት ቀጣይነት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ አንዱ ነው።

በሌላ በኩል የዚህ ፕሮጀክት ሁለተኛ ምዕራፍ (2nd phase) በዝግጅት ሂደት ላይ በመሆኑ በአፋጣኝ ማስጀመር እና በመጀመሪያው ምዕራፍ ያልተጠናቀቁትን ስራዎች በማካተት የጥራት መሰረተ ልማቱን ማጠናከር ይጠበቃል ነው ያሉት።
(የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት)

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia