Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Dec 19, 2025 .

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) እና የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) እና የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤት ጠንካራ የንግድ ማህበረሰብ ለመፍጠር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ(ተባባሪ ፕሮፌሰር) እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቢንያም ኤሮ ተፈራርመዋል።

 

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤት በኢትዮጵያ እና በዓለም ንግድና ኢንቨስትመንትን ማስተዋወቅ፤ ለንግድ ስራ አስቻይ ሁኔታ እንዲፈጠርማድረግ እንደሁም ነጋዴዎች የዓለም አቀፍ የገበያ ስርዓትን እንዲያውቁ በማድረግ ሀላፊነቱን ለመወጣት ጥረት እያደረገ መሆኑን ዋና ፀሃፊው ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ጂዲፒ የግሉ ዘርፍ አሁን ያለው ድርሻ 15 በመቶ ብቻ ነው ያሉት ዶ/ር ቀነኒሳ በሚቀጥሉት10 ዓመታት ውስጥ የዘርፉን ድርሻ ከ50 በመቶ በላይ ለማሳደግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመው ይህንን ታላቅ ተልዕኮውን ለማሳካት ደግሞ የሚዲያ አጋርነት ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቢኒየም ኤሮ በስምምነቱ ወቅት መንግስት የግሉ ዘርፍ ከምንጊዜውም በላይ እንዲጠናከር የፖሊሲ ሪፎርም ማድረጉን ተከትሎ የንግድ ገበያው ለዓለም ክፍት ሆኗል ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ህግና ስርዓት ተከትለው፤ ፈጠራዎቻቸውን አጎልብተው፤ በዓለም ላይ ተፎካካሪ እንዲሆኑ ኢቢሲ በሁሉም የመገናኛ አማራጮች አስተማሪ መረጃ  መስጠቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።

በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ ተቋማት በኢትዮጵያ ጠንከራና በዓለም ተወዳዳሪ የሆነ የግል ዘርፍ ተዋናዮችን ለመፍጠር ይሰራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia