Dec 24, 2025 .
አራተኛው ብሔራዊ ሀገር አቀፍ የሴቶች ኢኮኖሚ ማብቃት ፎረም በአዳማ ከተማ ተካሔደ፡፡



አራተኛው ብሔራዊ ሀገር አቀፍ የሴቶች ኢኮኖሚ ማብቃት ፎረም በአዳማ ከተማ ተካሔደ፡፡
ፎረሙ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዩ ኤን ውመን፣ አክሽን ኤድ ኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በመባበር የተዘጋጀ ነው፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የሴቶችን ኢኮኖሚ አቅም ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላትና የኢኮኖሚ ልማት ተቋማት ጋር ትስስር ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የ2030 የዘላቂ ልማት ግቦች አጀንዳን ለማሳካት የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቁልፍ ተግባር ሲሆን ለዚህም ሴቶችን ማበረታታት፣ መብታቸውን ማክበር እና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ይገባል ነው ያሉት፡፡
የሴቶችን የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ በክህሎት፣ በፋይናንስ፣ በመስሪያ ቦታና የገበያ ትስስር በመፍጠር ረገድ ችግሮችን ማቃለል የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑም በፎረሙ ላይ ተብራርቷል፡፡
ከፎረሙ ጎን ለጎን በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና በአዳማ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አስተባባሪነት በአዳማ ከተማ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ የተሠማሩ ሴቶች ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ለእይታ ያቀረቡ ሲሆን ሚኒስትሯና የፎረሙ ተሳታፊዎች ጎብኝተውታል፡፡

