Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Dec 25, 2025 .

በማዕድን ዘርፍ ባሉ መልካም እድሎችና እንቅፋቶች ዙሪያ ያተኮረ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

   

በማዕድን ዘርፍ ባሉ መልካም እድሎችና እንቅፋቶች ዙሪያ ያተኮረ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ ተካሄደ።
( ECCSA: 16/4/2018)
በአዲስ አበባ በሚካሄደው ወርክሾፕ ላይ የማእድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ብርሃኔ ያደሳ፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል መጋቢ ስርዓት ታየ ለታ፣ ዋና ጸሐፊው ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሠር)፣ የሳይፕ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ኃይለመለኮት አስፋው  እንዲሁም ከክልሎች የማዕድን ቢሮዎችና በዘርፉ የተሠማሩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ብርሃኔ ያደሳ በውይይቱ መክፈቻ ላይ እንደገለጹት መንግሥት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማምጣት ትኩረት ከሠጣቸው ዘርፎች አንዱ ማእድን መሆኑንና የዘርፉን ተጠቃሚነት ለማሣደግም በልዩ ትኩረት እየተሠራበት እንደሚገኝ አንሥተዋል።

ወርቅ፣ ፕላቲኒየም፣ የኢንዱሥትሪ ማዕድናት፣ የኢነርጂ ማዕድናት፣ ፔትሮሊየምና የመሣሠሉት ሀብቶች ቢኖሩም እሥካሁን በሠፊው ባለመሠራቱ ሀገራዊ ተጠቃሚነቱ አነስተኛ ሆኖ ቆይቷል ነው ያሉት።

ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ ( ተባባሪ ፕሮፌሠር) በበኩላቸው ሀገሪቱ ካሏት ጸጋዎች አንዱ የሆነው የማዕድን ሀብት በአግባቡ እንዲለማ ወርክሾፑ ለዘርፉ ለውጥ ትልቅ ሚና  እንዳለውና የማዕድን ንግድና ኢንቨሥትመንት እንዲስፋፋም ከቁፋሮ እሥከ ተጠቃሚነት ባለው የእሴት ሠንሠለት ምክር ቤቱ በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

የሳይፕ (Center for International Private Enterprise) ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ኃይለመለኮት አስፋው በበኩላቸው ሣይፕ የግሉ ዘርፍ እንዲጠነክር እየሠራ መሆኑን ጠቅሠው ድርጅቱ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ ማካከል ውይይቶች እንዲካሄዱ፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንዲሠጡና በሌሎችም ተግባራት ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ጋር በጋራ ሲስራ መቆየቱንና ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia