Jan 19, 2026 .
እ.ኤ.አ ከጥር 18 እስከ 20 2026 በዱባይ የሚካሄደው የአለማችን ትልቁ የቡና ኤግዚቢሽን (WORLD OF COFFEE DUBAI) ተከፍቷል።


እ.ኤ.አ ከጥር 18 እስከ 20 2026 በዱባይ የሚካሄደው የአለማችን ትልቁ የቡና ኤግዚቢሽን (WORLD OF COFFEE DUBAI) ተከፍቷል።
በዚህ ኤግዚቢሽን ላይም የኢትዮጵያ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢርን ጨምሮ የመንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የሀገራችን ቡና ላኪዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ቡና አምራቾች፣ ላኪዎች አልሚዎች እና እሴት ጭመራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች እየተሳተፋበት ሲሆን ኢትዮጵያ ስፔሻሊቲ ቡናዋን በዓለማቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ የሚያስችላት 𝐒𝐩𝐞𝐜𝐢𝐚𝐥𝐭𝐲 𝐂𝐨𝐟𝐟𝐞𝐞 𝐚𝐭 𝐖𝐨𝐫𝐥𝐝 𝐨𝐟 𝐂𝐨𝐟𝐟𝐞𝐞 𝐃𝐮𝐛𝐚𝐢 𝟐𝟎𝟐𝟔 በዱባይ የዓለም ንግድ ማዕከል የሚካሄድ ዝግጅት ነው፡፡
ለ5ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን የቡና ኢንዱስትሪው የመካከለኛው ምስራቅ ዋና መድረክ ሆኖ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የቡና አምራቾችን፣ አልሚዎችን፣ ቸርቻሪዎችን፣ ታላላቅ ነጋዴዎችን እና የኢንዱስትሪ ተዋናዮችን በማገናኘት ትልቅ ሚና ይኖረዋል ።

