Jan 22, 2026 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆብር የዋንጫ እና የወርቅ ደረጃ ምስክር ወረቀት ተሸለሙ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆብር የዋንጫ እና የወርቅ ደረጃ ምስክር ወረቀት ተሸለሙ።
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለክልሉ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የእውቅና ሽልማት መርሀ ግብር ሲካሄድ ሽልማቱን ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እጅ የተቀበሉት በ2017 ዓ.ም በከፍተኛ ተነሳሽነት የሚጠበቅባቸውን ግብር በመክፈል ታማኝ ግብር ከፋይ በመሆን ሀገራቸውን በማገልገላቸው ነው።
ሽልማቱ የግሉ ዘርፍ ሀገሩን ለማገልገል ቃል የሚገባበት መሆኑንም አቶ ሰብስብ ገልጸዋል።
የንግዱ ማኀበረሠብም በሰበሰበው ሀብት እና ገንዘብ ሳይሆን ለአገሩ ባደረገው ልዩ ልዩ አስተዋፆና በከፈለው ግብር መወዳደር እንዳለበትም አቶ ሰብስብ ተናግረዋል::
የትናንትናዋ፣ የዛሬዋ ኢትዮጵያም ሆነ የነገዋ ኢትዮጵያ የንግዱ ማህበረሰብ አሻራ ናት ሲሉ ሀሳባቸውን አስፍረዋል።

