Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jan 26, 2026 .

ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) በአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ስነ ምግብ አማካሪ ከሆኑት አቶ ከፍያለዉ ሙለታ ጋር በጽ/ቤታቸዉ መክረዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ሂደት ዉስጥ የግሉ ዘርፍ ሚና ምን መሆን በሚገባበት ሁኔታ ላይ በአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ስነ ምግብ አማካሪ ከሆኑት አቶ ከፍያለዉ ሙለታ ጋር በጽ/ቤታቸዉ መክረዋል።

የግሉ ዘርፍ ከግብርና እስከ  አግሮ ፖሮሰሲንግ  የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት  ባላቸዉ ዘርፎች የተሰማራ እንደመሆኑ መጠን  ስነ-ምግብ (Neutrition) በሚፈለገዉ ሁኔታ ለዜጎች ምቹ እንዲሆን በማድረግ ሂደት ዉስጥም የአንበሳዉን ድርሻ እንደሚይዝ በዉይይቱ ተነስቷል።

በዉይይቱ ላይ የተገኙት የናይል ሴንቸሪ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ፍቅሩ በቀለ በበኩላቸዉ የተስተካከለና ጤናማ ስነ-ምግብ ጤናማና ዕድገቱ የተስተካከለ አምራች ዜጋን ለማፍራት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዉ ይህንን ዕዉን ለማድረግ ደግሞ የግሉ ዘርፍ ሚና የጎላ ነዉ ብለዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia