ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በGIZ/AU ከGIZ Ethiopia AfCTASupport Component Lead ኦዲ ሎሬስ ጋር ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ የግሉን ዘርፍ አቅም በመገንባት በአህጉራዊና አለምአቀፋዊ ገበያ ዉስጥ ብቁ ተወዳዳሪ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በGIZ/AU ከGIZ Ethiopia AfCTASupport Component Lead ኦዲ ሎሬስ ጋር ተወያይተዋል።
ሁለቱ ወገኖች የተወያዩት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት መሪ የግሉ ዘርፍ ድምፅ እንደመሆኑ መጠን አገራችን ኢትዮጵያ በገባችበት ነአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና እና አባል ለመሆን ጫፍ በደረሰችበት የአለም የንግድ ድርጅት ዉስጥ የግሉ ዘርፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን አቅሙን ለመገንባት ባዘጋጀዉ ምክረ ሀሳብ ላይ ነዉ።
በምክረ ሀሳቡ ምክር ቤቱ ካቀረባቸዉ ዉስጥ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የፕሮቶኮል ስምምነት መሠረት የላኪዎችን ግንዛቤ ማሳደግ፣የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ሠራተኞችን አቅም መገንባት፣ የቢዝነስ ፎረሞችን ማዘጋጀትና የስልጠና ሞጁሎችን ማዘጋጀት የሚሉት በGIZ/AU በ2026 የበጀት ዓመት የቅድሚያ ትኩረት አግኝቷል።
እነዚህንም ከመግባባት የተደረሰባቸዉን የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ከስምምነት ተደርሷል።


Barreessaan Ol’aanaaMana Maree Daldalaafi Waldaalee Sekteraa Itoophiyaa Dr Qananiisaa Lammii haalaa gahumsa dhaabbilee dhuunfaa biyya keenyaa cimsuun Daldala sadarkaa Ardii Afrikaafi Idil- Addunyaa keessatti dorgomtoota taasisuun danda’urratti GIZ/AUtti hoggantuu, GIZ/Ethiopia Component Lead, Aude Lanois waliin mari’ataniiru.

