Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Mar 24, 2026 .

ለንግድና ዘርፍ ማኅበራት  ምክር ቤቶች አባላት የዲጂታል ማርኬቲንግና ኢ_ኮመርስ  ስልጠና እየተሰጠ ነው ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለንግድና ዘርፍ ማኅበራት  ምክር ቤቶች አባላት የዲጂታል ማርኬቲንግና ኢ_ኮመርስ  ስልጠና እየሰጠ ነው ።

የስልጠናው  ማስጀመሪያ  ላይ የተገኙት የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ፀሐፊ  ወይዘሮ  ሄለን ረታ  የምክር ቤቶች አባላት   ተለዋዋጭ በሆነው የቢዝነስ ዓለም ውስጥ ራሳቸውን ለውድድር ዝግጁ ማድረግ እንደሚገባቸው ገልፀዋል ።

ምክር ቤቱም የአባላትንና  የቢዝነስ ባለቤቶችን አቅም መገንባት ከተሰጡት ተልዕኮዎች አንዱ መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ዋና ፀሐፊዋ   አባላትም  ቢዝነሱ ለውጭ ክፍት መሆኑን  በመረዳት  ራሳቸውን በስልጠና ማብቃት እንደሚገባ ጠቁመዋል ።በመሆኑም  ተወዳዳሪ ሆኖ  ገበያው ላይ ለመቆየት  ቢዝነሳችሁን  በንግድ ክህሎት መመራት አለበት   ብለዋል ።

የምክር ቤቱ የቢዝነስ አመራር አካዳሚ ዳይሬክተር አቶ ብሥራት በለጠ በበኩላቸው የዲጂታል ማኬቲንግና ኢ ኮመርስ ስልጠና የቢዝነስ ባለቤቶች በሥራ ላይ  የሚገጥሟቸውን ተግዳሮች ለመፍታት በእጅጉ አጋዥ መሆኑን ገልጸው ምክር ቤቱ ስልጠናዎችን ከሰጠ በኋላ   የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች ለመፍታት የድጋፍ ና ክትትል ስራ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

 

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia