Dr. Aynalem Abayneh, Vice President of ECCSA, held a high-level meeting with a delegation from Azerbaijan


Dr. Aynalem Abayneh, Vice President of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), held a high-level consultative meeting with a delegation from Azerbaijan
The objective of the meeting was to strengthen the two countries’ trade and investment ties.
The Azerbaijani delegation included Ambassador Ruslan Nasibov, Ambassador of Azerbaijan to Ethiopia, the Executive Director of the Baku Business Center, and representatives from the Export and Investment Promotion Agency (AZPROMO).


During the discussion, Dr. Aynalem highlighted the ECCSA’s pivotal role in Ethiopia’s economic development and trade and investment promotion.
He briefed the delegation on the ongoing national economic reforms and pointed out lucrative investment opportunities in agriculture, mining, tourism, ICT and other, inviting Azerbaijani businesses to explore these opening sectors.
Yusif Abdullayev, Executive Director of the Baku Business Center at AZPROMO, expressed the strong interest of Azerbaijani companies in investing in Ethiopia, specifically noting the construction, mining, and digitization sectors.
Both parties emphasized that this engagement builds on the momentum of the Ethiopian Prime Minister’s recent visit to Azerbaijan. Mr. Abdullayev noted that economic cooperation must move hand in hand to ensure mutual benefits for both nations as they strengthen their strategic partnership.
ECCSA’s deputy secretary general, Ms. Helen Reta, management members and other Azerbaijani delegation members participated in the discussion.
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዓይናለም አባይነህ ከአዘርባጃን የልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም የሁለትዮሽ የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
የአዘርባጃን ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር ስላን ናሲቦቭ፣ የወጭ ንግድና ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ኤጀንሲ (AZPROMO) ተወካይ እና የባኩ ቢዝነስ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዩሲፍ አብዱላየቭ ያካተተ ነው፡፡
ዶ/ር ዓይናለም ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ልማት እና ንግድና ኢንቨስትመንት ማስፋፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ያለውን ወሳኝ ሚና አንስተዋል።
ስለ ሀገር አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለልዑካን ቡድኑ ማብራሪያ የሰጡት ዶክተር አይናለም በግብርና፣ በማእድን፣ በቱሪዝም፣ በአይሲቲ እና ሌሎችንም አዋጭ የኢንቨስትመንት እድሎችን ጠቁመው የአዘርባጃን ቢዝነሶች በእነዚህን ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡


የወጭ ንግድና ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ኤጀንሲ (AZPROMO) ተወካይ እና የባኩ ቢዝነስ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዩሲፍ አብዱላየቭ በበኩላቸው የአዘርባጃን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ያላቸውን ከፍተኛ ፍላጎት ገልጸው በተለይም የግንባታ፣ ማዕድንና ዲጂታይዜሽን ዘርፎችን ዋነኛ ትኩረት መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ አዘርባጃን ያደረጉት ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል በትብብር ለመስራት ከፍተኛ መነሳሳት መፍጠሩም ተገልጿል፡፡
ዩሲፍ አብዱላዬቭ የሁለቱም ሀገራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን ማሳደግ እንደሚተበቅባቸውም ገልጸዋል።
በውይይቱ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ፀሃፊ ወይዘሮ ሄለን ረታ እና ሌሎች የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ሌሎች የአዘርባጃን ልዑካን ቡድን አባላት ተገኝተዋል።

