Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Mar 27, 2026 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው “ኢትዮ ቻምበር የንግድና ኢንቨስትመንት ባዛር” በአዳማ ከተማ  ተከፈተ።

  

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው “ኢትዮ ቻምበር የንግድና ኢንቨስትመንት ባዛር” በአዳማ ከተማ  ተከፈተ።

የኢትዮጵያን ይግዙ! በሚል መሪ ሐሳብ በሚካሄደው ዝግጅት በቆዳ ውጤቶች፣ አልባሳትና የግብርና ምርቶችን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ አምራቾችና ነጋዴዎች ምርቶቻቸውን አቅርበዋል።

በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት  ኃላፊና የፕሬዚደንቱ ተወካይ አቶ ዋሲሁን ፍቅሬ ዝግጅቱ የንግዱ ማኅበራሠብ የገበያ እድል እንዲያገኝ፣ ምርቶች እንዲተዋወቁና ኢንተርፕራይዞችን ለመደገፍ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።

ዝግጅቱ በተለያዩ ምክንያቶች ቢዝነሳቸው የተቀዛቀዘባቸው ኢንተርፕራይዞች ቢዝነሣቸውን  ለማነቃቃት የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለውም አቶ ዋሲሁን ገልጸዋል።

የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ወይዘሮ ሔለን ረታ በበኩላቸው የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚው አንቀሣቃሽ እንደመሆኑ ምርቶችን በጥራትና በብዛት እንዲያመርት፣ በሥራ እድል ፈጠራ፣ በቴክኖሎጅ ሽግግር መሪ ተዋናይ እንዲሆን ምክር ቤቱ በትኩረት ይሠራል ብለዋል።

ባዛሩ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ሸማቹ ማህበረሠብ ጥራት ያላቸውን የሀገር ውስጥ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገዛ እና አምራቹም ምርቱን በቀላሉ ለሸማቹ እንዲያቀርብ እድል የሚፈጥር መሆኑ ተጠቁሟል።

በመክፈቻ ፕሮግራሙም ከአዳማ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣ ከአዳማ ከተማ ኢንቨሥትመንት ግሩፕ፣ ከአዳማ ከተማ የሥራ እድል ፈጠራና ክህሎት ጽህፈት ቤት የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎችና የኤግዚቢሽንና ባዛሩ የመክፈቻ ስነ-ስርዐት  ተሣታፊዎችና እንግዶች ተገኝተዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia