በአቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የተመራ የኢትዮጵያ የንግድ ማኅበረሰብ በጣሊያን ረሚኒ የአትክልት እና ፍራፍሬ ኤግዚብሽን ላይ ተሳትፎ እያደረገ ነው።


በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የተመራ የኢትዮጵያ የንግድ ማኅበረሰብ በጣሊያን ረሚኒ በተጀመረው የአትክልት እና ፍራፍሬ ኤግዚብሽን (MAK FRUT 2026 RIMINI EXPO ITALY – Frut & VEG PROFESSIONAL SHOW) ላይ ተሳትፎ እያደረገ ነው።
እ.ኤ.አ ከኤፕሪል 21- 23/2026 በሚካሄደው በዚህ ኢግዚቢሽን ላይ የሚሳተፈውን የኢትዮጵያን የንግድ ልዑክ በቆይታው በንግድ ትስስር ፣ ምርቶችን በማስተዋወቅ እና የልምድ ልውውጥ እንደሚያደርግም ፕሬዚደንቱ ገልፀዋል ::
በዚህ መርሐ ግብር ላይ ሮም የሚገኘው ኢምባሲያችን ፤ ኢትዮጵያዊያን ተሳታፊዎችን በመቀበል፣ የምርት ማሳያ ቦታን በማመቻቸት እና ለኢትዮጵያ ምርት የገበያ ትስስር መፍጠር የሚቻልበት የንግድ ለንግድ ዉይይቶችን ማመቻቸቱን የገለፁት ፕሬዚደንቱ ፦
በተጨማሪም፦ ኢምባሲው ከዘርፉ ጋር በተያያዘ የማምረቻ መሳርያ ፈላጊዎችን ከአምራች ኢንዳስትሪዎች ጋር በማገናኘት ትልቅ እገዛ እያደረገ ነው ሲሉ አክለዋል::
በመጨረሻም በዚህ በጣሊያን ለኢትዮጵያ ኢምባሲ አመራሮች እና ሚሲዮን አባላት በንግዱ ማኅበረሰብ፣ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና በራሴ ስም
በአገራችን ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲያድግ እንዲሁም የአገራችን ምርት በሰፊው እንዲተዋወቅ እያደረጋችሁት ላለው ተግባር ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉ አጠቃለዋል።




The Ethiopian business community, led by Sebsib Abafira Abajobir, President of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations, is participating in the horticulture and fruit exhibition taking place in Rimini, Italy, Macfrut 2026 (Frut & Veg Professional Show).
Speaking about the exhibition, which is being held from April 21–23, 2026, the President noted that the Ethiopian business delegation is engaging in business networking, promoting Ethiopian products, and exchanging experiences during its stay.
He further explained that Ethiopia’s Embassy in Rome has been facilitating the participation by welcoming Ethiopian delegates, arranging exhibition spaces, and organizing business-to-business (B2B) meetings that create market linkage opportunities for Ethiopian products.
In addition, he highlighted that the Embassy is providing significant support by connecting those seeking production machinery with relevant manufacturing industries.
In conclusion, the President expressed his appreciation, on behalf of the business community, the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations, and himself, to the leadership and staff of the Ethiopian Embassy in Italy for their efforts in promoting Ethiopia’s trade and investment and in enhancing the international visibility of Ethiopian products.

