የሴቶች፤ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች የፋይናንስ አካታችነት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ለተገኛችሁ በሙሉ መልካም የተሳትፎ ጊዜ እንዲሆንላችሁ መልዕክቴ ይድረሳችሁ፡- ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

ዛሬ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ም/ቤት በተዘጋጀው የሴቶች፤ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች የፋይናንስ አካታችነት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ለተገኛችሁ በሙሉ መልካም የተሳትፎ ጊዜ እንዲሆንላችሁ መልዕክቴ ይድረሳችሁ፡፡
በአጠቃላይ የፋይናንስ አቅርቦት ምንነት ፤ የሴቶች፤ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነት በግሉ ዘርፍ እንቅስቃሴ ላይ የሚኖረው አንደምታ፣ በአሁኑ ወቅት በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ በኩል በመከናወን ላይ ስላሉ ተግባራት እና ሌሎች ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት እንደምታደርጉ እንዲሁም በቀጣይ ተጨባጭ ለውጥእንደምታስመዘግቡ እምነቴ ነው፡፡
በዚህ አጋጣሚም ለዚህ ፎረም መሳካት ድጋፍ ላደረጉልን ድርጅቶች በሙሉ ምስጋናዬን እያቀረብኩኝ ለወደፊቱም ለግሉ ዘርፍ ዕድገት አብረን እንደምንሰራ አረጋግጣለሁ፡፡
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት




Today, I would like to extend my message wishing you all a productive and engaging time as you participate in the financial inclusion awareness forum for women, youth, and persons with disabilities, organized by the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations.
I believe that you will have a meaningful discussion focusing on the overall concept of financial access, the role and benefits of inclusion for women, youth, and persons with disabilities in private sector activities, as well as the ongoing efforts being undertaken by both the government and the private sector, along with other key issues that require attention.
I am also confident that this dialogue will lead to tangible outcomes and practical changes in the near future.
I would like to express my appreciation to all partner organizations that have contributed to the success of this forum, and I reaffirm our commitment to continue working together for the growth of the private sector.

