Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jun 15, 2026 .

የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ይፋዊ የሕዝብ ውይይት መድረክ የኢትዮጵያ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ታክስ ከፋዩን ማህበረሰብ (የግሉን ዘርፍ) በመወከል ተሳትፎ አድርጓል።

በዛሬው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን ፤በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ይፋዊ የሕዝብ ውይይት መድረክ  አካሂዷል።

በዚህ የውይይት መድረክም ፤ የኢትዮጵያ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ታክስ ከፋዩን ማህበረሰብ (የግሉን ዘርፍ) በመወከል ተሳትፎ አድርጓል።

እንደሚታወቀው፤ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 341/95 ከተሰጡት  ኃላፊነቶች ወካከል የግሉን ዘርፍ በመወከል:- በሚወጡ የንግድና ኢንቨስትመንት ነክ ፖሊሲዎች፣ አዋጆች፣ ደንብ እና መመሪዎች ላይ  በጥናት እና አድቮኬሲ ስራዎቹ በተገኙ ውጤቶች መነሻ አስተያየት እና የህግ ግብዓት ማቅረብ  ዋንኛው ነው።

በዚህ መነሻም በዛሬው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008ን ለማሻሻል በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ የግብዓት ማሰባሰቢያ የባለድርሻ አካላት መድረክ ላይ በመገኘት መስተካከል፣ መሻሻል እና መካተት  ያለባቸው ጉዳዮችን የተመለከቱ ሀሳቦች  በአጽንኦት  አንስተናል።

በመሆኑም ቋሚ ኮሚቴው በምክር ቤታችን በረቂቅ አዋጁ እንዲካተቱ ፣እንዲስተካከሉ ፣ እንዲለወጡ ወይም ቀሪ እንዲሆኑ የቀረቡ አስተያየቶችን ትኩረት ሰጥቶ በመውሰድ የአዋጁ አካል እንደሚያደርግ እምነታችን ነው።

በዚህ አጋጣሚም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የግሉ ዘርፍ መብቶችና ጥቅሞች መከበር የሚያደርገውን ሁሉ- አቀፍ   ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል እናረጋግጣለን።

ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት

Today, the Standing Committee for Planning, Budget, and Finance Affairs of the House of Peoples’ Representatives held a public consultation forum on the draft amendment to the Federal Tax Administration Proclamation.

At this consultation forum, the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) participated as a representative of the taxpayer community, particularly the private sector.

As is well known, among the responsibilities entrusted to ECCSA under Proclamation No. 341/2003 is the mandate to represent the private sector by providing comments and legal inputs on trade- and investment-related policies, proclamations, regulations, and directives based on the findings of its research and advocacy activities.

Accordingly, during today’s stakeholder consultation forum on the draft proclamation prepared to amend the Federal Tax Administration Proclamation No. 983/2016, we actively presented recommendations on provisions that require revision, improvement, inclusion, or reconsideration.

We therefore believe that the Standing Committee will give due consideration to the comments and recommendations submitted by our Chamber regarding provisions that should be incorporated, amended, revised, or removed from the draft proclamation and that these inputs will be reflected in the final law.

On this occasion, we would also like to reaffirm that the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations will continue to strengthen its comprehensive efforts to safeguard and promote the rights and interests of the private sector.

Sebsib Abafira Abajobir
President, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia