የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡


የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን ተፈራረሙት የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አስማረ መለሰ ናቸው፡፡
ሁለቱ ተቋማት በግሉ ዘርፍ እና ዩኒቨርሲቲ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከርና ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃብት ለማፍራት እንዲሁም ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ የቢዝነስ ተቋማት ጋር ተወዳዳሪ የግል ዘርፍ እንዲኖር እንደሚሰሩ ተብራርቷል፡፡
የኢንዱስትሪውንና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ትስስር ጠንካራ ለማድረግ ምክር ቤቱ በተለይም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዩኒት በማቋቋም እየሰራ ሲሆን ከደብረ ብርሃን ዩኒሲቲ ጋር የተፈረመው ስምምነትም ይህንን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያግዛል ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት በመጠናቀቅ ሂደት ላይ መሆን፣ የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነት መተግበር፣ የብሪክስ አባልነትና ሌሎችም ክፍለ አህጉራዊ ግንኙነቶች መጠናከር የግሉ ዘርፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን ገፊ ምክንያቶች ናቸው፡፡
ለዚህም በእውቀት ላይ የተመሰረተ የንግድና ኢንቨስትመንት ስራዎች እንደሚያስፈልጉና ከትምህርት ተቋማት ጋር ያለን ትብብር ማጠናከር አስፈላጊ ነው፡፡
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ የንድፈ ሀሳብ ብቻ ሳይሆን የተግባር ክህሎት እንዲኖራቸው የግሉን ዘርፍ ከሚወክለው የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር ስምምነት መፈራረሙ ትልቅ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሁለቱ ተቋማትም ስምምነቱን ተግባራዊ በማድረግ አርዓያነት ያለው ሀገራዊ ስራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን በፕሮግራሙ ላይ አረጋግጠዋል፡፡
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተግባር ተኮር ተብለው ከተለዩ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሲሆን ቢዝነስና ኢኮኖሚ አንዱና ዋነኛው የትኩረት መስክ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ፣ የአድቮኬሲና የግሉ ዘርፍ አቅም ግንባታ ስራዎች ዋነኛ ዓላማዎቹ ሲሆኑ መንግስትንና የግሉን ዘርፍ የማቀራረብ ሚና ያለው ምክር ቤት ነው፡፡

Manni Maree Daldalaafi Waldaalee Sektera Itoophiyaa Yuunivarsitii Dabrabirhaan waliin walii galtee waliin hojjechuu mallatteesse.
Waliigalticha kan mallatteessan Barreessaa ol’aanaa mana marichaa Dr Qananiisaa Lammiifi pireezidaantii Yuunivarsitichaa Dr Asmaaree Laggasaa yoo ta’an, kaayyoon walii galtichaas Yuunivarsitichu humna namaa fedhii dhaabbilee dhuunfaa guutuufi gabaarratti barbaadamu horachuurratti xiyyeeffatee hojjechuuf Mana Daldalaafi Waldaalee Sektera Itoophiyaa, sagalee dhaabbilee dhuunfaa ta’ee waliin qindoominaan hojjechuu akka ta’es hoggantoonni dhaabbilee lamaanii ibsaniiru.
Dhaabbileen dhuunfaa biyya keenyaa dorgommii akka idil-addunyaafi ardii Afrikaatti isaan eggatuuf qophii ta’uu qabu. Kanaafimmoo humna namaa.beekumsa ammayyaa gonfate qabaachuun murteessaa ta’uun ibsameera. Kanaafi fedhii dhabbilee dhuunfaa Manni Marichaa haala qabatamaa irratti hundaa’uun adda baasu irratti xiyyeefachuun sirna barnoita isaaniin walsimsiisuuf qophii ta’us Dr Asmaareen ibsaniiru.

