የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ከምክር ቤታችን ጋር ለመስራት ላሳያችሁት ተነሳሽነት ምስጋናዬን አቀርባለሁ:- ሰብስብ አባፊራ

ዛሬ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ምክር ቤታችን በተለያዩ ጊዜያት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ ከአቻ የንግድ ምክር ቤቶች፤ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደጋቸው
የመግባቢያ ስምምነቶች አንኳር ግብ፤ የምናከናውናቸው ንግድና ኢንቨስትመንትን የማስፋፋት እንዲሁም የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ተሳትፎ የማሳደግ ተግባራችንን በጋራ ስራዎች ውጤታማ ማድረግ ነው።
በመሆኑም ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጋራ የተፈራረምነው የመግባቢያ ስምምነት ውጤታማነት የሚለካውም ከላይ ባስቀመጥኳቸው አጠቃላይ ግቦች አንፃር ሲሆን ፤ የምክር ቤታችን የስራ ኃላፊዎችም የከዚህ ቀደሞቹን ጨምሮ ዛሬ የተፈራረምነው ስምምነት በአጭር ፣ በመካከለኛና ረዥም ጊዜ ሊያሳኳቸው ያስቀመጧቸውን የተናጠል እና የጋራ ተግባራትን ውጤታማነት በየጊዜው በመፈተሽ የግሉ ዘርፍ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ሁኔታ እንደምትፈጥሩ እምነቴ ነው ፡፡
በመጨረሻም የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ከምክር ቤታችን ጋር ለመስራት ላሳያችሁት ተነሳሽነት ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት
Today, the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) and Debre Berhan University signed a Memorandum of Understanding (MoU) that will enable them to work together in partnership.
At various times, our Chamber has entered into Memoranda of Understanding with other chambers of commerce, government and non-government stakeholders, as well as higher education institutions.
The primary objective of these agreements is to enhance the effectiveness of our efforts to promote trade and investment and to increase the participation of the private sector in the economy through collaborative initiatives.
Accordingly, the effectiveness of the MoU we have signed with Debre Berhan University will be measured against these overarching goals. I am confident that the officials and staff of our Chamber will continuously assess the effectiveness of both the individual and joint activities outlined under this agreement, as well as previous agreements, in the short, medium, and long term. Through regular evaluation and follow-up, I believe they will ensure that tangible benefits are delivered to the private sector.
Finally, I would like to express my sincere appreciation to the leadership of Debre Berhan University for the initiative and commitment you have demonstrated in partnering and working with our Chamber.
Sebsib Abafira Abajobir
President, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

