Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jul 04, 2026 .

“አረንጓዴ አሻራ የዛሬ ተግባራችን፣ የነገ ትውልድ ዋስትናችን ነው:- ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

  

አረንጓዴ አሻራ ለዘላቂ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ!

በዛሬው ቀን የሀገር አቀፍ፣  የክልል እና የከተማ ምክር ቤቶች በከፊል የተሳተፉበት የዳይሬክተሮች ቦርድ ልዑካን ቡድን  በጅማ ከተማ  የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በንጉሥ አባጅፋር ቤተመንግስት ግቢ ያደረጉ ሲሆን ከተማዋ ውስጥ የተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶችንም ጎብኝተዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብርን ሰኔ 8/2018 ዓ.ም ” ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በይፋ  ማስጀመራቸው ይታወሳል።

ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በዚሁ ወቅት፣ ዘንድሮ የተያዘውን የ8 ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል ግብ ለማሳካት በሚደረገው ብሔራዊ የንቅናቄ ስራ ላይ ‎በሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለተግባራዊነቱ እንዲረባረቡ ባቀረቡት  ጥሪ መሠረት  በዛሬው ዕለት  የመጀመሪያ ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራማችንን በጅማ ከተማ የአባ ጅፋር ቤተ መንግስት አስጀምረናል ::

በመላው አገራችን የምትገኙ 516 የክልል፣ የከተማ እና የወረዳ ንግድ ምክር ቤቶች አመራር እና ሰራተኞች እንዲሁም ባለሀብቶች የ8ቢልየን ችግኝ ተከላ መረሀ ግብሩን ለማሳካት ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርባለው ::

መላው የንግዱ ማህበረሰብ ለሀገራዊው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ስኬት በግንባር ቀደምነት የራሱን ድርሻ እንዲወጣም ከታላቅ አደራ ጭምር ጥሪዬን አቀርባለው።

“አረንጓዴ አሻራ የዛሬ ተግባራችን፣ የነገ ትውልድ ዋስትናችን ነው።”

ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia