የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዛሬ ለላኪዎች በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት (AfCFTA) ዝግጁነት ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዛሬ ለላኪዎች በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት (AfCFTA) ዝግጁነት ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ።
በአጠቃላይ የአፍሪካ አህጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጣና ከሚያስገኛቸው እድሎች በላቀ መልኩ ተጠቃሚ ለመሆን እንዲቻል በላኪነት የተሰማሩ አምራቾችና ላኪዎች የንግድ ስምምነቱ ስላቀፋቸው የስምምነት ይዘቶች በቂ መረጃ ሊኖራቸው ይገባል፤ ከዚህ አንፃር የንግዱ ማህበረሰብ መረጃዎችን በቅርበት እንዲያገኝ ምክር ቤታችን እየሰራ ነው።
በተጨማሪም፤ ከስምምነቱ አፈፃፀም ጋር ተያይዞ መንግስት ንግድና ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ረገድ በግሉ ዘርፍ ለሚሰሩ ሥራዎች ድጋፍ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
በሌላም በኩል፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናው የሚሰጠውን የገበያ እድል ለመጠቀም የፈፃሚውንም ሆነ የተቋማትን አቅም መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡
በዚህ ረገድ የሀገር ውስጥ ምርቶች ነባራዊ ሁኔታ ላይ ዝርዝር ጥናት በማድረግ ላኪዎች ወደ አፍሪካ ሀገራት ገበያ የሚልኳቸው ምርቶች ሊያሟሉ የሚገባቸውን መስፈርቶች እና ዝርዝር ሁኔታዎችን በተመለከተ በቂ ስልጠና ሊሰጥ ይገባል፡፡ የዛሬው ስልጠናችንም የዚህ አካል ነው።
በመሆኑም የስልጠናው ተሳታፊዎች ሰፊ ተሳትፎ እንድታደርጉ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
በመጨረሻም ለኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ለ ጂ አይ ዜድ አፍሪካ ህብረት (GIZ AU) እንዲሁም ስልጠናውን እየሰጡ ላሉት የዘርፉ ባለሙያዎች ምስጋናዬን አቀርባለሁ ።
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት
The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations is currently providing training for exporters focused on readiness for the African Continental Free Trade Area (AfCFTA) agreement.
In general, to fully benefit from the wide range of opportunities created by the AfCFTA, producers and exporters engaged in export activities need to have sufficient knowledge of the provisions of the agreement. In this regard, our Chamber is working to ensure that the business community can access relevant information more closely and in a timely manner.
In addition, in relation to the implementation of the agreement, the government should support private sector efforts by further expanding trade and investment.
On the other hand, effectively utilizing the market opportunities created by AfCFTA requires strengthening the capacity of both implementing bodies and institutions.
In this regard, it is important to conduct detailed studies on the current status of domestic products and provide adequate training on the standards and requirements that exporters must meet when supplying products to African markets.
Today’s training is part of these ongoing efforts. I therefore encourage all participants to actively engage in the training.
Finally, I would like to express my appreciation to the Ministry of Trade and Regional Integration of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, GIZ Africa Union (GIZ AU), and the experts currently delivering this training.
Sebsib Abafira Abajobir
President, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

