Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jul 04, 2026 .

የአፍሪካ ቀንድ የዲጂታል ገበያ ትስስር (Horn of Africa Digital Market Integration – HDMI) ፕሮጀክት 3ኛ ዙር የአመራር ኮሚቴ ስብሰባ በደቡብ ሱዳኗ ጁባ ተካሄደ ።

የአፍሪካ ቀንድ የዲጂታል ገበያ ትስስር (Horn of Africa Digital Market Integration – HDMI) ፕሮጀክት 3ኛ ዙር የአመራር ኮሚቴ ስብሰባ በደቡብ ሱዳኗ ጁባ ተካሄደ ።

በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያን የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊና የኢጋድ (IGAD) ቢዝነስ ፎረም ሰብሳቢ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ ተሳትፎ እያደረጉ ነው።

በዚህ የ3ኛ ዙር የአመራር ኮሚቴ ስብሰባ
ከአባል ሀገራት የተውጣጡ ተወካዮችን ጨምሮ የዘርፋ ምሁራን እና የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላትን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን በውይይቱም በአፍሪካ ቀንድ ዲጂታል ለውጥን ለማፋጠንና የክልላዊ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት ይካሄዳል።

በመድረኩ የግሉ ዘርፍና የመንግስት ተወካዮችን፣ የልማት አጋሮችን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በማሰባሰብ የፕሮጀክቱን አፈጻጸም ለመገምገም እና የበለጠ የተሳሰረ፣ ተወዳዳሪ እና ዘመናዊ የክልሉ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለመወሰን ያለመ ነው።

ተሳታፊዎቹ በተለይም የዲጂታል ገበያ ልማትን ማፋጠን፣ ድንበር ተሻጋሪ ንግድን ማቀላጠፍ፣ የክልሉን የእሴትና አቅርቦት ሰንሰለት ማሻሻል፣ እንዲሁም ፈጠራን፣ ኢንቨስትመንትን እና አሳታፊ ኢኮኖሚያዊ እድገትን የሚደግፉ ፖሊሲዎችን ማጎልበትን ታሳቢ ያደረገ ነው ።

በተጨማሪም የዲጂታል ትስስርን ማሻሻል፣ የቁጥጥር ማዕቀፎችን ማጣጣም እና ቢዝነሶች ከተሳሰረ ገበያ የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችሉ አማራጮችንም የሚያመላክት ነው።

ፕሮጀክቱ የዲጂታል ኢኮኖሚውን አቅም ለማሳደግ፣ የንግድ እንቅፋቶችን ለመቀነስ ብሎም መሠረተ ልማትን ለማጠናከር እና በአገራቱ መካከል ትብብርን ለማስፋፋት የተቀረጸ ነው።

The Third Horn of Africa Digital Market Integration (HDMI) Project Steering Committee meeting has convened in Juba, South Sudan, bringing together representatives from member states and key regional stakeholders to accelerate digital transformation and deepen economic integration across the Horn of Africa.

The high-level forum serves as a platform for governments, the private sector, development partners, and academic institutions to review the progress of the HDMI Project and chart the way forward in building a more integrated and competitive regional digital economy.

Discussions are focused on advancing digital market development, enhancing cross-border trade facilitation, strengthening regional value and supply chains, and promoting policies that support innovation, investment, and inclusive economic growth.

Participants are also exploring ways to improve digital connectivity, harmonize regulatory frameworks, and expand opportunities for businesses to benefit from a regional market.

Representing the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), Secretary General Dr. Kenenisa Lemi, who also serves as Chair of the IGAD Business Forum, is participating in the meeting.

His participation underscores the private sector’s growing role in shaping regional economic integration and advancing a business-friendly digital ecosystem across the Horn of Africa.

The HDMI Project is regarded as a key regional initiative aimed at unlocking the potential of the digital economy by reducing barriers to trade, improving digital infrastructure, and fostering greater collaboration among countries in the region.

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia