ስልጠናዎች የማስፈፀም አቅም ማጎልበቻ ናቸው፡፡:- ሰብስብ አባፊራ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት እንዲሁም ከንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤቶች ለተወጣጡ ባለሙያዎች ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠናዎችን የማስፈፀም አቅም ማጎልበቻ የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ነው።
ቀደም ባሉት መልዕክቶቼ እንደገለፅኩት የአቅም ግንባታ ስራዎቻችን ግብ የግሉ ዘርፍ ተዋንያን ባገኙት እውቀት እና ክህሎት ታግዘው ቢዝነሶቻቸውን የበለጠ የሚያስፋፉበት በይበልጥም በስራ ዕድል ፈጠራና ምርታማነት ተሽለው የሚገኙበት ሁኔታን መፍጠር ነወ።
በመሆኑም እየተሰጠ ያለው ስልጠና የግሉን ዘርፍ ክፍቶች የሚሞላ መሆን ያለበት ሲሆን፤ የዛሬው የአሰልጣኞች ስልጠና ተሳታፊዎችም ለንግዱ ማኅበረሰብ በቀጣይ የምትሰጡት አቅም ግንባታ ስራ በዚህ መልኩ የተቃኘ እንደሚሆን እምነቴ ነው።
በዚህ አጋጣሚም መልካም የስልጠና ጊዜ እንዲሆንላቸሁ እመኛለሁ።
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት





ECCSA has launched a three-day Training of Trainers program, beginning today, for professionals from various government institutions, private sector organizations, and chambers of commerce and sectoral associations.
As I have emphasized in my previous messages, the main objective of our capacity building initiatives is to empower private sector actors with the knowledge and skills they need to expand their businesses, enhance productivity, create more employment opportunities, and contribute more effectively to economic development.
Accordingly, the training being delivered should address the key capacity gaps within the private sector.
I am confident that the participants of this Training of Trainers program will, in turn, provide impactful capacity building programs that effectively respond to the needs of the business community.
On this occasion, I would like to wish all participants a productive, successful, and rewarding training experience.
Sebsib Abafira Abajobir
President, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

