የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ምክር ቤቶች በራሳቸው አቅም ስራዎቻቸውን የበለጠ እንዲያጎለብቱ ማድረግ ይችላሉ፡-ሰብስብ አባፊራ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር ለክልሉ ቦርድ አባላት ፣ ለከተማ ም/ቤቶችና ማህበራት የተዘጋጀ የአባላት ጉዳይና የንግድ ለንግድ (B2B) ትስስር የምክክርና የስልጠና መድረክ አካሂዷል።
በተጨማሪም ፤ የኦሮሚያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የምዕራብ ኦሮምያ 3ተኛ ክላስተር የአቅም ግንባታ ስልጠና በአምቦ ጀምሯል።
እንደሚታወሰው፦ የግሉ ዘርፍ ጉዳዮች ዙሪያ የተዘጋጁ መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን፤ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች፣ ክላስተሮች እና ከተሞች እየሰጠን ሲሆን፦ በነዚህ የአቅም ግንባታ ስራዎቻችንም የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የቦርድ አመራሮች እና የፅህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የመንግስትና የግል ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም በዋንኛነት የንግዱ ማኅበረሰብ ተሳታፊ እየሆነ ነው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተከናወኑ ያሉ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎቻችን ቀሪ ማሻሻል ያሉብን ተግባራት እንደተጠበቁ ሆነው፤ ከተደራሽነት አንፃር ስፉት እያገኙ የመጡ መሆኑ፣ የስልጠና ርዕሰ ጉዳዮቻችን ወቅታዊና ትኩረት የሚሹ የግሉ ዘርፍ ጉዳዮች እየሆኑ መምጣታቸውና በተቋማዊ እቅድ መመራታቸው እንዲሁም የአባል ምክር ቤቶች ተሳትፎ እያደገ መምጣቱ ለውጤታማነታችን ማሳያ ነው።
ከዚህ ባለፈ ግን የሰልጣኞችን ቁጥርም ሆነ ስብጥር ማሳደግ፣ አካታችን የበለጠ ማጎልበት(strengthen inclusiveness)
፣ የስልጠናዎች መደራረብን ለመቀነስ ጥረት ማድረግ፣ ከስልጠናው የተገኙ ውጤቶችን የምንከታተልበት ስረዓት መዘርጋት የሚኖርብን ሲሆን፤ አባል ምክር ቤቶችም በራሳቸው አቅም እያከናወኑ ያሉ ስራዎቻቸውን የበለጠ እንዲያጎለብቱ ከስራዎቻችን ጋር የበለጠ ማስተሳሰር እና እገዛ ማድረግ ይጠበቅበናል።
በመጨረሻም ፤ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በተመለከተ ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎችን በተገቢው ሁኔታ ከተገበርን ደጋግመን እንደምንለው የግሉ ዘርፍ የሚጠበቅበትን ብቻ ሳይሆን ከሚጠበቅበት በላይ ማበርከት በሚችልበት አቋም ላይ እንዲገኝ ማድረግ እንችላለን።
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት
The Central Ethiopia Regional Chamber of Commerce and Sectoral Association, in collaboration with the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations, conducted a consultation and training forum on membership affairs and Business-to-Business (B2B) linkages for the region’s board members, city chambers, and sectoral associations.
In addition, the Oromia Chamber of Commerce and Sectoral Association launched the 3rd cluster capacity-building training program for Western Oromia in Ambo.
As is well known, similar capacity-building trainings focusing on private sector issues are being conducted across different regions, clusters, and cities, including Addis Ababa.
These programs bring together board leaders and secretariat heads of chambers of commerce and sectoral associations, representatives of public and private institutions, and, most importantly, members of the business community.
The capacity-building initiatives carried out in recent months have demonstrated encouraging progress. While there are still areas requiring improvement, the programs have significantly expanded their outreach, addressed timely and priority issues affecting the private sector, been implemented in line with institutional plans, and witnessed growing participation from member chambers. These developments reflect the increasing effectiveness of our efforts.
At the same time, further work is needed to increase both the number and diversity of trainees, strengthen inclusiveness, minimize duplication of training programs, establish a robust system for monitoring the outcomes of the trainings, and provide greater support to member chambers so they can further enhance the initiatives they are implementing with their own capacities by aligning them more closely with our institutional activities.
Finally, if we effectively implement the strategic directions we have set for these capacity-building programs, we can enable the private sector not only to fulfill its expected role but also to make contributions that exceed expectations, thereby strengthening its role as a driving force for Ethiopia’s economic development.
Sebsib Abafira Abajobir
President, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

