Jul 06, 2026 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ተወዳዳሪ የሆነ የሰዉ ኃይል ማፍራት በሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች ላይ በአዳማ ከተማ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ማስተባበርያ ክፍል የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት በገበያ ላይ ተፈላጊ እና ተወዳዳሪ የሆነ የሰዉ ኃይል ማፍራት በሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች ላይ በአዳማ ከተማ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።
ስልጠናዉ የማሰልጠኛ ተቋማቱ የሚሰጡትን ስልጠና እና የኢንዱስትሪዎች የቅጥር ፍላጎትን ማጣጣም ላይ ያተኮረ ሲሆን ስልጠናዎቹ በተጨባጭ ሊለኩ የሚችሉ ክህሎቶችን የሚያጎናፅፉ መሆን እንዳለባቸዉም በስልጠናዉላይ ተገልጿል።
ስልጠናዉ ተቋማቱ በሚቀርጿቸዉ የስልጠና ካሪኩለሞቹ ዉስጥ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማጠናከር እና የተመራቂዎችን የሥራ ዕድል በማሳደግ፣ የኢንዱስትሪዎች የሰለጠኑ ሠራተኞችን እጥረት በመፍታት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የኢንዱስትሪ ዕድገትን እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን ለማረጋገጥ ታስቦ የተዘጋጀ ነዉ።
ይህ ስልጠና የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከGIZ/STEP4 ባገኘዉ የፋይናንስ ድጋፍ ያቋቋመዉን የኢንዱስትሪና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ትስስር የሚያስተባብር የስራ ክፍል ዓላማን ለባለድርሻ አካላት ለማስተዋወቅም ጭምር ታስቦ በም/ቤቱ እና GIZ/STEP4 ትብብር የተዘጋጀ ነዉ።
