Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jul 23, 2026 .

የምክር ቤታችን የ2018 ዓ.ም. የዕቅድና  የአፈጻጸም የግምገማ መድረክ ውጤቶቻችን በጥልቀት የተገመገሙበት ነው፡- አቶ ሰብስብ አባፊራ

የምክር ቤታችን የ2018 ዓ.ም. የዕቅድና  የአፈጻጸም የግምገማ መድረክ ውጤቶቻችን በጥልቀት የተገመገሙበት፣ ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች ይበልጥ ለማጠናከርና  የታዩ ድክመቶችንና ተግዳሮቶችን በግልጽ ለይተን ተገቢ የማሻሻያ እርምጃዎችን ያስቀመጥንበት፣ ለ2019 ዓ.ም. የሥራ ዘመን ተጨባጭና ውጤታማ አቅጣጫዎችን በጋራ የተወሰነበት ጠቃሚ መድረክ መሆኑን የም/ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አስረድተዋል።

የ2018 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸማችንን ልዩ የሚያደርገው ምክር ቤቱ ተቋማዊ አቅሙን በዘላቂነት ለማጎልበት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከሌሎች  ሚኒስቴር መስራያ ቤቶች፣ ከውጭ ሀገር ኤምባሲዎች፣ ከተለያዩ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮቻችን እንዲሁም በየደረጃው ከሚገኙ የክልል ም/ ቤቶቻችን ጋር ባደረግነው ከፍተኛ ቅንጅት  የተጣለበንን ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት የሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ኢኒሼቲቮችንና የለውጥ አቅጣጫዎችን በመቅረጽ ያከናወነው ሁለንተናዊ ተቋማዊ የሪፎርም ሥራ አመርቂ ነበርም ብለዋል። በዚህ ሂደት ምክር ቤቱ አስተዳደራዊ፣መዋቅራዊና ኦፕሬሽናል አቅሙን በማጠናከር ራሱን በተሻለ ሁኔታ አደራጅቶ፣ ለቀጣይ እድገቱ ጠንካራ መሠረት የጣለና ተልዕኮውን በውጤታማነት ለመፈጸም ዝግጁ የሆነ ተቋም መሆን ችሏል።
በዚህ ጠንካራ ተቋማዊ መሠረት ላይ በመቆምም፣ ምክር ቤቱ ለሀገራችን የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ስኬት የሚያበረክታቸዉ  በርካታ ተግባራትን በብቃት አከናውኗል፤ ይህንንም አጠናክረን እንቀጥላለን።
በተለይም  ም/ቤታችን ንግድና ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት፣ ለሀገር ውስጥ ምርቶች አዳዲስ የዓለም ገበያ መዳረሻዎችን በማፈላለግ፣ የገበያ ትስስርንና የቢዝነስ ለቢዝነስ (B2B) ግንኙነቶችን በማጠናከር፣ የኤክስፖርት ዕድሎችን በማስፋትና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎን በማጎልበት ተጨባጭ ውጤቶችን አስመዝግቧል።
 

በተመሳሳይም በም/ቤታችን የቢዝነስ አመራር  አካዳሚ፣ በጥናትና አድቮኬሲ፣ በአባላት ጉዳዮች፣ በኮሙኒኬሽን፣ በሕግና ግልግል፣ በአስተዳደር ሥርዓት በማጠናከር ፣ በህንፃ መልሶ ማልማትና የገቢ ምንጫችንን በማጠናቀር እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ድምፅ በሀገራዊ የፖሊሲና የኢኮኖሚ ልማት ሂደቶች ውስጥ የሚኖረንን  ሚና በማጠናከር ከፍተኛ ውጤቶችን አስመዝግበናል። በሁሉም የሥራ ዘርፎች የተቀመጡ የዕቅድ ግቦችን በከፍተኛ ደረጃ በማሳካት የ2018 የበጀት ዓመትን ውጤታማና ተስፋ ሰጪ አፈጻጸም አስመዝግቧል።

በመሆኑም የ2018 ዓ.ም. የሥራ ዘመን ለምክር ቤታችን በተቋማዊ ለውጥ፣ በአገልግሎት ጥራት፣ በአባላት ተጠቃሚነት፣ በሀገራዊ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ አስተዋጽኦና በግሉ ዘርፍ ተወካይነት የታዩ ውጤቶች ለቀጣይ እድገታችን ጠንካራ መሠረት የጣሉ እና በብዙ መለኪያዎች ልዩ የስኬት ዓመት እንደነበር ግምገማችን አረጋግጧል።

በቀጣይ ትኩረት የሚሹና በያንዳንዱ የሥራ ዘርፍ ያስመዘገብናቸውን ውጤቶች እንደ መነሻ በመውሰድ፣ ያሉብንን ክፍተቶችና ተግዳሮቶች በቅንነት በመገምገም፣ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜትና በጋራ ትብብር መንፈስ ለመፍታት በትጋት መሥራት ይኖርብናል። ይህም ምክር ቤቱን የበለጠ ጠንካራ፣ ተወዳዳሪ፣ ዘላቂና ለቀጣይ ትውልድ የሚተላለፍ ተቋም ለማድረግ የሚያስችለን ይሆናል የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል ፕሬዚዳንቱ።

በሚቀጥለው የ2019 በደት ዓመት ሀገራዊ ንግድና ዘርፍ  ም/ቤታችንን በይበልጥ ለማዘመን እና ድርብ ድል በማስመዘገብ የተወከልንበትን የንግዱን ማህበረሰብ ሁለንትናዊ መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ተቋማችን በአሠራር ፣ በቴክኖሎሎጂና በዲጅታላይዜሽን በይበልጥ ለማዘመን እንዲሁም ተደማጭና ከሀገር አልልፎ በአህጉር እና  በዓለም አቀፍ መድረኮች ተፅኖ ፈጣሪ እንዲሆን አመርቂ ሥራ መሥራት ይጠበቅብናል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia