Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jul 30, 2026 .

ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በሩዋንዳ የግል ፌደሬሽን በኪጋሊ ከተማ በተዘጋጀዉ አለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ላይ ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በሩዋንዳ የግል ፌደሬሽን በኪጋሊ ከተማ በተዘጋጀዉ አለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ላይ ተሳትፈዋል።

ከንግድ ትርኢቱ ጎን ለጎን   በአፍሪካ ነፃ አህጉራዊ የንግድ ቀጣና በሴቶች ለሚመሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ዕድሎችን ማስፋት በሚል መሪ ቃል በተካሄደዉ የምክክር መድረክ ላይ ዶ/ር ቀነኒሳ ፓናሊስት/ተናጋሪ/ ነበሩ።

በዚህ የምክክር መድረክም ላይ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና በሚፈጠሩ የገበያ ዕድሎች በሴቶች የሚመሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ለማድረግ የመንግስት፣ የንግድ ምክር ቤቶችና የልማት አጋሮች ቅንጅትና ትብብር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የቢዝነሶችን የተወዳዳሪነት አቅም ከመገንባት አንፃር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በቢዝነስ አመራር አካዳሚዉ በኩል እየሰራ ያለዉን ስራም እንደ ተሞክሮ አጋርተዋል።

በሩዋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ መስፍን ገብረማርያም  በንግድ ትርኢቱ  ላይ ተገኝተዉ  ባስተላፉት መልዕክት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የገበያ ዕድሎችን አሟጦ ለመጠቀም የአባል አገራት ትብብር ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia