Aug 04, 2026 .
የተከልናቸው ዛፎች እና የፍራፍሬ ችግኞች ፀድቀውና አድገው ፍሬ እስከሚያፈሩ ድረስ ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ አረንጓዴ ኃላፊነታችንን በጽናት የምንወጣ ይሆናል

ተስፋን እንተከል!
በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ መርሃ ግብር ከሸገር የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቦርድ አመራር እና ሰራተኞች እንዲሁም ከሽገር ከተማ አመራሮች እና ከሱሉልታ አካባቢ ነጋዴዎች ጋር በመሆን ደማቅ የአረንጓዴ አሻራችንን በሱሉልታ አኑረናል።
ይህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለንግዱ ዘርፍ የጎላ ኢኮኖሚያዊ ትርጉም አለው። ዛሬ የተከልናቸው የፍራፍሬ ችግኞች አካባቢን ከመንከባከብና ከማልማትም ባሻገር፤ የሀገራችንን አጠቃላይ ንግድ አቅም ለማሳደግና የውጭ ምንዛሬ ግኝታችንን ከፍ ለማድረግ የነገ ተስፋዎቻችን ናቸው።


በዛሬው ዕለት የተከልናቸው ዛፎች እና የፍራፍሬ ችግኞች ፀድቀውና አድገው ፍሬ እስከሚያፈሩ ድረስ ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ አረንጓዴ ኃላፊነታችንን በጽናት የምንወጣ ይሆናል።
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት

