Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Aug 21, 2026 .

ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ የድሬዳዋ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትን መደገፍና ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር ዉጤታማ ዉይይት አካሂደዋል።

 

የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ የድሬዳዋ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትን መደገፍና ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር ዉጤታማ ዉይይት አካሂደዋል።
የድሬዳዋ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ቀደም ሲል እንደ ኢትዮጵያ ከተመሠረቱ አንጋፋ የአገር አቀፍ ንግድ ም/ቤት ቅርንጫፎች አንዱ ሆኖ ሳለ እና ድሬዳዋ የምስራቁ የአገራችን ክፍል ነፃ የንግድ ቀጣና፣ ትልቅ የኢንዱስትሪ ዞን፣ የደረቅ ወደብና የባቡር ጣቢያ ያለባት የንግድ መዳረሻ ሆኖ እያለች የንግድ ም/ቤቷ በጣም መዳከሙ ተገቢ አለመሆኑን ዶ/ር ቀነኒሳ ለከተማ አስተዳደሩ አመራሮች አብራርተዋል።


አሁን መንግስት ለግሉ ዘርፍ ከሰጠዉ ትኩረትና የግሉ ዘርፍ ለአገር የኢኮኖሚ ዕድገት የሚጠበቅበትን እንዲያበረክት መንግስትንና የግሉን ዘርፍ የሚያገናኝ፣ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋና ምቹ የንግድ ከባቢ እንዲፈጠር የአዲቮኬሲ ስራዎችን የሚሰራ ጠንካራ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት መኖር እንዳለበትም አስረድተዋል።
ያለ ግሉ ዘርፍ ተሳትፎ የአገር ኢኮኖሚ በሚፈለገዉ ልክ አያድግም፤ ጠንካራ የግል ዘርፍ ተሳትፎ እንዲኖር ደግሞ ጠንካራ የንግድ ምክር ቤት መኖር አለበት ያሉት ዋና ፀሐፊዉ፣ ይህ እንዲሆን ደግሞ መንግስት የንግድ ም/ቤቶችን እንደ አጋዥ አቅም አይቶ አስፈላጊዉን ድጋፍ ማድረግ አለበት ብለዋል።
የድሬዳዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በበኩላቸዉ የከተማ አስተዳደሩ ከከተማዉ የንግድ ቢሮ ጋር በመሆን የንግድ ም/ቤቱን እንደ አዲስ የማደራጀት ስራ ቢሰራም አሁን ያለን የንግድ ም/ቤት ከተማችንን የሚመጥን አይደለም፤ ስለሆነም ከተማዋ እንደ አገርም የምስራቁ በር የኢኮኖሚ ማዕከል እንደመሆኗ መጠን ጠንካራና የንግዱ ማህበረሰብ እዉነተኛ ድምፅ ሊሆን የሚችል ም/ቤት በአዲስ መልክ በሰዉ ኃይልና በሎጂስቲክ ለማደራጀት ኃላፊነቱን እንወስዳለን ብለዋል።
የድሬዳዋ ከተማ የንግድ ም/ቤት የነበረዉ ህንፃ አስተዳደሩ ለሌላ አገልግሎት በማዋሉ ለረጅም ጊዜ ሲነሳ የነበረዉ የይመለስልን አለያም ምትክ ይሰጠን ጥያቄም በአሁኑ ወቅት ምላሽ አግኝቶ መሬትና የህንፃ መስርያ ብር 200 ሚሊዮን ብር በከተማ አስተዳደሩ መፈቀዱንም ምክትል ከንቲባዉ አስታዉቀዋል።
በዉይይቱ ላይ የከተማ አስተዳደሩ የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመን ቢሮ የንግድ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሚኑ ጠሃ፣ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አብዱሰላም መሀመድ፣ የከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር አልይ እና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት የምስራቅ ዲስትሪክት ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አትክልት ጥላሁን ተሳትፈዋል።
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመንግስት አደረጃጀት የከተማዉ የንግድ፣ኢንዱስትሪና ኢንቨስተመንት የሚመበምክትል ከንቲባዉ እንደመሆኑ መጠን መጨረሻም የድሬዳዋ ከተማ ንግድ ም/ቤትን መልሶ የሚያደራጅ በከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊዉ የሚመራና የገቢዎችና የንግድ ቢሮ ኃላፊዎች በአባልነት የተካተቱበት ኮሚቴን ምክትል ከንቲባዉ አቋቁመዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia