Aug 25, 2026 .
እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ:- ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የመቻቻል እሴቶቻችንን በበለጠ የምናድስበት እንዲሁም መልካም ተግባሮቻችንን የምናጠናክርበት ነው።
በመሆኑም ለመላው ሙስሊም የንግዱ ማኅበረሰብ እና ሕዝብ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የደስታና የበረከት እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ።
ሰላም፦ የልማትና የእድገት መሠረት ነው። ስለሆነም የመውሊድ በዓል የሚያስተምረንን መቻቻል፣ መረዳዳትና አብሮነት በተግባር በማጠናከር፣ ለሰላማዊ እና ለለማች ኢትዮጵያ የየራሳችንን አስተዋጽኦ እንድናበረክት በዚሁ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
መልካም የመውሊድ በዓል!
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

