አገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና አስተዳደር ምክር ቤት ምስረታ ተካሄደ::


አገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና አስተዳደር ምክር ቤት ምስረታ በአዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን፤ በምስረታውም ከሥራና ክህሎት፣ ከገንዘብ ፣ ከትምህርት፣ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ከሌሎች ተቋማት የተውጣጡ ተወካዮች፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና ከግሉ ዘርፍ የባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ምክር ቤቱ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ የፖሊሲና የአመራር አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ፣ ስትራቴጂያዊ የመፍትሔ ሀሳቦችን ለማቅረብ እና የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ መዋቅራዊ ትብብርን ለማጠናከር የሚሠራ መሆኑ ተገልጿል።

የክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮዎች ተወካዮችም በምክር ቤቱ ውስጥ የተወከሉ ሲሆን፣ የሚዲያ ተቋማትና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮችም በምክር ቤቱ አወቃቀር እንዲካተቱ ተደርጓል።
የምክር ቤቱ መዋቅር በፌዴራል ደረጃ ብቻ የሚወሰን ሳይሆን፣ በክልል ደረጃ እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጆች ደረጃ የሚሠራ መዋቅር እንደሚኖረው ተገልጿል።
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርነት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና የኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌዴሬሽን የምክር ቤቱ ሴክሬታሪያት መሆናቸውም በምስረታው ላይ ተገልጿል።
❇️❇️❇️❇️
The National Technical and Vocational Education and Training (TVET) Governance Council has been established to strengthen coordination, governance, and stakeholder engagement in Ethiopia’s TVET sector.
The establishment of the Council took place at the Radisson Blu Hotel in Addis Ababa, bringing together representatives from the Ministry of Labor and Skills, Ministry of Finance, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations, Ministry of Education, Ministry of Industry, and other government institutions, as well as private sector stakeholders.
The Council will play a key role in providing policy and strategic directions for the TVET sector, proposing strategic solutions to sectoral challenges, and strengthening structured collaboration between the government and the private sector.
The Council’s structure will will also operate at the regional level and within TVET colleges, creating a coordinated governance framework across different levels of the TVET system.
Under the leadership of the Ministry of Labor and Skills, ECCSA and the Ethiopian Employers’ Federation will participate in the Council’s activities at the secretariat level.

