Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 22, 2026 .

ሕገ-ወጥ ንግድ ሕጋዊ የንግድ ድርጅቶችን ከማዳከሙም ባሻገር መንግሥት የሚሰበስበውን ገቢ ያሳጣል- ሰብስብ አባፊራ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፤ ንግድና ኢንቨስትመንትን የማስተዋወቅ፣ ግልጽና ተወዳዳሪ የንግድ ስርዓት እንዲኖር የመደገፍ፣ ስነ-ምግባራዊ የንግድ አሠራርን የማጠናከርና በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል እንደ አገናኝ ድልድይ ሆኖ የማገልገል ኃላፊነት ያለበት ከመሆኑ አንጻር ዛሬ ሕገወጥ ንግድን በመከላከል ዙሪያ የተካሄደው መድረክ ችግሮቹ ላይ በመወያየት የጋራ የመፍትሄ አቅጣጫ በመተለም ረገድ ትልቅ ሚና ይኖረዋል።

ሕገ-ወጥ ንግድ ሕጋዊ የንግድ ድርጅቶችን ከማዳከሙም ባሻገር መንግሥት የሚሰበስበውን ገቢ ያሳጣል፣ የአገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስትመንትን ያዳክማል እንዲሁም ሙስናን በማስፋፋት በንግድ ድርጅቶች መካከል የሚኖር ውድድርን የሚያዛባ ሲሆን ፤ የድንበር ቁጥጥርን በማዳከምም ሕዝቡ በተቋማት ላይ ያለውን አመኔታም እንዲያጣ ያደርጋል።

ከዚህም ባሻገር የሕጋዊ ንግድ ተቋማትን ብቻ የሳይሆን ሸማቾችን፣ መንግሥትን፣ ሠራተኞችን፣ አምራቾችንና አጠቃላይ ኢኮኖሚውን የሚነካ ጉዳይ ነው።

በመሆኑም ፤ ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በማካሄድ ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የኤክስፖርት ተወዳዳሪነትንና የኢንዱስትሪ ሽግግርን ለማጎልበት በትጋት በምትሠራበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ ሕገ-ወጥ ንግድ ለአገራዊ ልማት ከባድ ፈተና ሆኖ የዘለቀ በመሆኑ መከላከሉ ትኩረት ያሻዋል።

በዚህ አጋጣሚም፤ ኮንትሮባንድ ወይም ሕገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።

ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia