የማዕድን ዘርፍ ለምንፈልገው የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው-ሰብስብ አባፊራ

በማዕድን ዘርፍ ዙሪያ ያሉ መልካም ዕድሎች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ የመንግስትና የግሉዘርፍ የውይይት መድረክ(PPD) የማዕድን ሚኒስቴር እንዲሁ ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እና ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ተካሂዷል ፡፡
እንደሚታወቀው የማዕድን ዘርፍ በአገራችን ከግብርና፣ ከማኑፋክቸሪንግ፣ ከICT፣ ከቱሪዝም እና ከሌሎች በመንግስት ቅድሚያ ከተሰጣቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎች አንዱ ከመሆኑም ባሻገር ለምንፈልገው የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው።
ዘርፉ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ቅድሚያ ከተሰጣቸው የኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ ልማት ዘርፎች አንዱ በመሆኑ ወይም ማዕድን የተፈጥሮ ሀብት ስለሆነም ብቻ ሳይሆን፣ ማዕድን ወደ ኢንዱስትሪ፣ የውጭ ንግድና የውጪ ምንዛሬ ገቢ እንዲሁም ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ኢንዱስትሪ ልማት እና ሰፊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚቀየር ጭምርም ከመሆኑ አንፃር በመንግስትና የግሉ ዘርፍ ትኩረት ማግኘቱ የሚጠበቅ ነው።
በመሆኑም ምክር ቤታችን ለዘርፍ ዕድገትና ለውጥ ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ፡፡
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
❇️❇️❇️❇️❇️
A Public Private Dialogue(PPD) focusing on the opportunities and challenges in Ethiopia’s mining sector was held in the presence of representatives from the Ministry of Mines, relevant stakeholders, and supporting institutions.
As is well known, the mining sector is one of Ethiopia’s priority investment sectors, alongside agriculture, manufacturing, ICT, tourism, and other strategic areas. Beyond this, the sector holds significant strategic importance for advancing the economic transformation the country aspires to achieve.
The importance of the mining sector goes beyond its role as a natural resource and a priority area for investment and economic development. When effectively developed and utilized, the sector can contribute significantly to industrial development, export growth and foreign-exchange earnings, job creation, and broader economic development.
It is therefore essential for the sector to receive sustained attention and coordinated support from both the government and the private sector.
In this regard, I would like to reaffirm that our Chamber will further strengthen its engagement and collaboration with relevant stakeholders to support the growth, development, and transformation of Ethiopia’s mining sector.
Sebsib Abafira Abajobir
President, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

