Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 01, 2026 .

በተመድ ግዥና የገበያ ዕድሎች ላይ ያተኮረ ሴሚናር በአዲስ አበባ ተካሄደ::

በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና ከሌሎች የተባበሩት መንግሥታት ተቋማት ጋር በመተባበር፣ በተመድ ግዥና የገበያ ዕድሎች ላይ ያተኮረ የአንድ ቀን ሴሚናር በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።

መርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አይናለም አባይነህ፣ የኢትዮጵያ ነጋዴዎች በተመድ የግዥ ዕድሎች ውስጥ የበለጠ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠንካራ አጋርነትን፣ ውጤታማ ክትትልን እና ተግባራዊ አፈጻጸምን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

የሴሚናሩ ዓላማ የተመድ የግዥ ስርዓቶችን፣ መስፈርቶችን እና የግዥ ዕድሎችን በተመለከተ ለንግዱ ማኅበረሰብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ ሲሆን፣ በአፍሪካ አህጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጣና ስር ያሉ የንግድ ዕድሎች እንዲሁም ንግዶች ከተመድ ስርዓት ጋር በተግባር ሊተሳሰሩ ስለሚችሉባቸው መንገዶች ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይትም ተካሂዷል።

A one-day business seminar on UN procurement and market opportunities is being held in Addis Ababa by the UN Economic Commission for Africa (UNECA), in collaboration with the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) and other UN agencies.

Opening the seminar, ECCSA Vice President Dr. Aynalem Abayneh stressed the need for stronger partnerships, effective follow-up and implementation to increase Ethiopian businesses’ participation in UN procurement.

The seminar covers UN procurement procedures and opportunities, while also highlighting business prospects under the African Continental Free Trade Area (AfCFTA). A panel discussion is also being held on practical ways businesses can engage with the UN system.

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia