ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በኢትዮጵያ የሜክሲኮ አምባሳደር አሌሃንድሮ ኢቬስ ኢስቴቪል ካስትሮ ከተመራ የንግድ ልዑክ ጋር ተወያዩ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በኢትዮጵያ የሜክሲኮ አምባሳደር አሌሃንድሮ ኢቬስ ኢስቴቪል ካስትሮ ከተመራ የንግድ ልዑክ ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸውም በሁለቱ አገራት መካከል የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቢዝነስ ለቢዝነስ ትብብር ለማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ ተነጋግረዋል። በልዑካን ቡድኑም የሜክሲኮን የወጭ ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ የሚሰራው COMCE እና በማዕድን ዘርፍ የተሰማራው GLG RECURSOS ኩባንያ ይገኙበታል።
ዋና ፀኃፊው በኢትዮጵያ ስላሉ የንግድና የኢንቨስትመንት ዕድሎች እንዲሁም ለውጭ ኢንቨስትመንት ምቹ አካባቢ ለመፍጠር መንግሥት ባከናወናቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርም ስራዎች ዙሪያ አብራርተውላቸዋል። አምባሳደር አሌሃንድሮ ኢቬስ ኢስቴቪል ካስትሮ በበኩላቸው የሜክሲኮ ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ አጋሮች ጋር አብረው እንዲሰሩና ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንዲሁም በሁለቱ አገራት መካከል የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስርን ኤምባሲው ሚናውን እንደሚወጣ ገልጸዋል።
የሜክሲኮ ኩባንያዎቹ ከኢትዮጵያ ገበያ በተጨማሪ ወደ ሰፊው የአፍሪካ ገበያ ለመግባት እንደ መግቢያ ለመጠቀም ኢትዮጵያ ተመራጭ ሀገር ስለመሆኗም አንስተዋል። የየሀገራቱ ንግድ ምክር ቤቶችም የንግድ ለንግድ (B2B) ትብብር ለማጠናከር፣ የኢንቨስትመንት አጋርነትንና የንግድ ልውውጥን ለማሳደግ በጋራ መስራት እንዳለባቸውም ተጠቁሟል።


The Secretary General of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), Dr. Kenenisa Lemie, has met Mexico’s Ambassador to Ethiopia, Alejandro Ives Estivill Castro, and a delegation of Mexican businesses to discuss ways to strengthen trade and investment ties.
The delegation included representatives of the Mexican Council of Foreign Trade (COMCE) and GLG RECURSOS, a mining company, among others.
The Secretary General briefed the delegation on Ethiopia’s investment and trade opportunities and ongoing economic reforms aimed at improving the business environment.
The Mexican delegation also discussed the potential for using Ethiopia as a gateway to wider African markets. The meeting highlighted the importance of business-to-business cooperation, with ECCSA and Mexican business organisations expected to support stronger commercial links and investment partnerships between the two countries.

