Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 02, 2026 .

የክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና በራሴ ስም እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ – ሰብስብ አባፊራ

የአማራ፣ የሶማሌ፣ የሲዳማ እና የጋምቤላ ክልሎች ምክር ቤቶች ባካሄዱት የመንግሥት ምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ የየክልሎቹን ርዕሰ መስተዳድሮች መሰየም  ተከትሎ፣ ክቡር አቶ አረጋ ከበደ፣ ክቡር አቶ ሙስጠፋ ሙሀመድ፣ ክቡር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ እና ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ የየክልሎቻችሁን የአመራርነት ኃላፊነት በመረከባችሁ በመላው የግሉ ዘርፍ፣ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና በራሴ ስም እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

በዚህ አጋጣሚም ፤ ክልሎቻችሁ ያላቸውን ሰፊ የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የምርት አቅም በማሳደግ፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማጠናከር፣ የስራ ዕድልን በማስፋፋት እና ዘላቂና አካታች የኢኮኖሚ ዕድገትን በማፋጠን የሚጠበቅባችሁን ኃላፊነት በብቃትና በስኬት እንደምትወጡ ያለኝን እምነት እገልጻለሁ።

የክልሎቻችሁን የኢኮኖሚ አቅም በተጨባጭ ውጤት ለመቀየር፣ የግሉን ዘርፍ እንደ ዋና የኢኮኖሚ እድገት አጋር በማጠናከር እና ለንግድና ለኢንቨስትመንት ምቹ፣ ተወዳዳሪና ቀልጣፋ የስራ አካባቢ በመፍጠር ረገድ የሚኖራችሁ አመራር ወሳኝ ነው።

በዚህ ረገድ፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፤  ከየክልሎቹ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ጋር በቅርበትና በተቀናጀ መልኩ በመስራት፣ ለግሉ ዘርፍ ምቹ የንግድ ስራ ከባቢ ለመፍጠር፣ ኢንቨስትመንትንና ንግድን ለማስፋፋት፣ የንግድና የኢኮኖሚ ትስስር ለማጠናከር እና የግሉ ዘርፍ ያለውን የልማት አስተዋጽኦ የበለጠ ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት  ላረጋግጥ እወዳለሁ።

በመጨረሻም፣ ክቡራን ርዕሰ መስተዳድሮች፣ በአዲሱ የአመራር ዘመናችሁ ለሕዝቦቻችሁ እና ለክልሎቻችሁ የላቀ ውጤት የምታስመዘግቡበት፣ ለንግድና ለኢንቨስትመንት የተሻለ ዕድል የምትፈጥሩበት እና የኢኮኖሚ ዕድገትንና የስራ ዕድልን በሚያፋጥን መልኩ ውጤትን የምታስመዘግቡበት የስኬት ዘመን እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ።

ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia