Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 05, 2026 .

አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ከምክር ቤቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ወ/ሮ ሙሉ ሰሎሞን ጋር ተወያዩ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ከምክር ቤቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ወ/ሮ ሙሉ ሰሎሞን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በምክር ቤቱ የስራ እንቅስቃሴና የለውጥ ተግባራት ዙሪያ ተነጋግረዋል፡፡

አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን በፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ለነበራቸው አስተዋጽኦ ያመሰገኑት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር በተሰሩ የሪፎርም ስራዎች የተገኙ ተቋማዊ ውጤቶችንና የንግድ ምክር ቤቶችን ለማጠናከር እየተሰሩ ባሉ ጉዳዮች ዙሪያ አብራርተውላቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የምክር ቤቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንቶችና አመራሮች የተቋሙ አምባሳደሮች በመሆን በልምዳቸውና በእውቀታቸው ምክር ቤቱን ማገዝ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን በበኩላቸው ባካበቱት ልምድና እውቀት ምክር ቤቱን በቅርበት ለማገዝና ከተቋሙ ጋር በትብብር ለመሥራት ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።

ከውይይቱ በኋላ ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ እና አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን የታደሰውን የምክር ቤቱን ሕንፃ በመዘዋወር የጎበኙ ሲሆን አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞንም ምክር ቤቱን ለማጠናከር በተከናወኑ ሥራዎችና በተገኙት ውጤቶች መደሰታቸውን ገልጸዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia