የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የተመራ የልዑካን ቡድን የሶማሊላንድ አስተዳደር ኢንሹራንስ ባለስልጣን ባዘጋጀው የሶማሌላንድ አስተዳደር የኢንሹራንስ ጉባዔና ኤክስፖ 2026 ላይ ለመሳተፍ ሀርጌሳ ገብቷል።

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የተመራ የልዑካን ቡድን የሶማሊላንድ አስተዳደር ኢንሹራንስ ባለስልጣን ባዘጋጀው የሶማሌላንድ አስተዳደር የኢንሹራንስ ጉባዔና ኤክስፖ 2026 ላይ ለመሳተፍ ሀርጌሳ ገብቷል።
ከጥቅምት 2-3ቀን 2019 በሀርጌሳ በሚካሄደው በዚህ ጉባዔና ኤክስፖ ላይ በአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በተለይም በንግድ ኮሪደሮች፣ በትራንስፖርት መረቦች፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሠረተ ልማትና በድንበር ተሻጋሪ ንግድ ዙሪያ ኢንሹራስ በሚኖረው ሚና ላይ ሰፊ ውይይት ይካሄዳል።
በመድረኩም ጠንካራና ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ የኢንሹራንስ አሰራር ለማሳለጥ የሚያስችሉ አስቻይ ሁኔታዎች ላይ ከመግባባት ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል።
በኢንሹራንስ ጉባዔና ኤክስፖ መክፈቻም የግሉን ዘርፍ በመወከል የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ከተያዘው መርሐ ግብር ለማወቅ ተችሏል።
በዚህ ጉባኤና ኤክስፖ የኢንሹራንስ ድርጅቶች፣ የኢንሹራንስ ተቆጣጣሪ ተቋማት፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የንግድ መሪዎች፣ ኢንቨስተሮች፣ የልማት አጋሮችና ሌሎች ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ይገኛሉ።

A delegation led by H.E. Sebsib Abafira Abajobir, President of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), has arrived in Hargeisa to participate in the Somaliland Insurance Conference and Expo 2026, organized by the Somaliland Administration’s Insurance Authority.
The conference and expo, scheduled to take place in Hargeisa on October 12–13, 2026, will provide a platform for extensive discussions on the role of insurance in economic activities across the Horn of Africa, particularly in trade corridors, transport networks, investment, infrastructure development, and cross-border trade.
The event is expected to build consensus on the enabling conditions needed to strengthen the insurance system and make it more conducive to investment. According to the scheduled programme, H.E. Sebsib Abafira Abajobir, President of ECCSA, will deliver a message on behalf of the private sector during the opening ceremony of the conference and expo.
The event will bring together insurance companies, insurance regulatory authorities, financial institutions, business leaders, investors, development partners, and other key stakeholders.

