የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና የካይዘን የልህቀት ማዕከል ስትራቴጅክ ትብብር ይፋ ሆኗል፡፡


የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና የካይዘን የልህቀት ማዕከል ስትራቴጅክ ትብብር ይፋ ሆኗል፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከካይዘን የልህቀት ማዕከል ጋር በመተባበር ለምክር ቤቱ የዳይሬክተሮች ቦርድና ለአባል ም/ቤቶች አመራሮች በካይዘን ፍልስፍና እና በአመራር ላይ ሲሰጥ የነበረዉ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ ከአመራሮች የጀመረዉ ስልጠና እስከ ም/ቤቶች ፈፃሚ ባለሙያዎች እና በሂደትም ለንግዱ ማህበረሰብ ለማዳረስ ከአጋር ድርጅቶች ጋር ይሰራል ብለዋል። የሁለቱ ተቋማት የስትራቴጂክ ትብብር ስኬት የሚለካዉ በሚሰጡ የስልጠና ብዛት ሳይሆን ከስልጠናዉ በኋላ በሚገኝ ተጨባጭ ለዉጥና ለአገር ኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋፅዖ በሚያደርግ የሚቆጠር ተግባር መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።

በካይዘን የልህቀት ማዕከል የተቋማት ትስስር ስታንደርዳይዜሽንና ኳሊቲ አሹራንስ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ደነቦ መኩሪያ፣ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና በካይዘን የልቀት ማዕከል የስትራቴጂክ ትብብር ማዕቀፍ ዉስጥ የሚሰሩ የአንድ አመት የስትራተጂክ አጋርነት ትብብር ዝርዝር ተግባራትን አቅርበዋል፡፡::
በአንድ አመት ጊዜ ዉስጥ የተመረጡ ኢንዱስትሪዎች ጉብኝትና የልምድ ልዉዉጥ ማካሔድ፣ ለ24 አሰልጣኞች በካይዘን ልህቀት ማዕከል የስልጠና ተቋም ዉስጥና በኢንዱስትሪዎች ዉስጥ በተግባር በማሰልጠን የብቃት ማረጋገጫ ያላቸዉ ብቁና የካይዘን አማካሪ ሊሆኑ የሚችሉ አሰልጣኞችን ለማፍራት እና እስከ 200 ለሚሆኑ ቢዝነሶች ስልጠና ለመስጠት መታቀዱን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አይናለም አባይነህ በስልጠናዉ ማጠናቀቂያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ለዉጥ ከራስ እንደሚጀምር በመግለፅ፣ በየደረጃዉ ያሉ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤቶች አመራሮች ከዚህ ስልጠና ባገኙት የካይዘን ፍልስፍና ግንዛቤ በመነሳት በአመራር ዘይቤአቸዉና በተቋማቸዉ ላይ ለዉጥ ማምጣት እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።

