ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማኅበራት ጥምረት ተወካይ ጋር በትብብር፣ የጋራ ሥራዎችና የዲያስፖራ ኢንቨስትመንት ዕድሎች ዙሪያ ተወያዩ።

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማኅበራት ጥምረት ተወካይ ጋር በትብብር፣ የጋራ ሥራዎችና የዲያስፖራ ኢንቨስትመንት ዕድሎች ዙሪያ ተወያዩ።
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማኅበራት ጥምረት የቦርድ አባል አቶ ማህሙድ መሐመድና የቡድናቸው አባላት በተሳተፉበት በዚህ ውይይት በዲያስፖራውና በኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስፋትና የንግድ ትብብርን ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር።
ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ለኢትዮጵያ ዲያስፖራ ያሉትን የኢንቨስትመንት ዕድሎች በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች አብራርተዋል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግና ከሀገር ውስጥ ንግዶች ጋር የንግድ ግንኙነት ለመፍጠር ለሚፈልጉ የዲያስፖራ አባላት ምክር ቤቱ ያለውን የድጋፍ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
የጥምረቱ ተወካዮችም በዓለም የተለያዩ ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኢንቨስትመንት፣ በእውቀትና ክህሎት ሽግግር፣ በሥራ ፈጠራ እና በንግድ ትስስር የሀገራቸውን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማገዝ ያላቸውን ጉልህ ሚና አንስተዋል።
ከምክር ቤቱ ጋር በቅርበት በመሥራት በተለያዩ ዘርፎች ከኢትዮጵያ ቢዝነሶች ጋር የጋራ የንግድ ዕድሎችን ለመፍጠር ያላቸውን ፍላጎትም ገልጸዋል።
በውይይቱ ላይ የግሎባል ዲያስፖራ ጂቡቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ነኢማ-ፊልሰን ዓሊን ጨምሮ ሌሎች የዲያስፖራ ኮሚዩኒቲ አባላት ተሳትፈዋል።

The Secretary General of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), Dr. Kenenisa Lemie, held a meeting with representatives of the Ethiopian Diaspora Associations Consortium to discuss opportunities for cooperation, joint initiatives, and diaspora investment in Ethiopia.
The meeting brought together Dr. Kenenisa Lemie, Mr. Mahmud Mohamed, a board member of the Ethiopian Diaspora Associations Consortium, and members of the consortium’s team.
The discussion focused on strengthening collaboration between ECCSA and diaspora organizations to promote investment, business partnerships, and private-sector development.
During the meeting, Dr. Kenenisa briefed the team on the investment opportunities available to Ethiopians living abroad across various economic sectors.
He also reaffirmed ECCSA’s commitment to supporting diaspora members interested in investing in Ethiopia and establishing business relationships with local enterprises.
Mr. Mahmud Mohamed highlighted the important role of the Ethiopian diaspora worldwide in contributing to the country’s economic development through investment, knowledge and skills transfer, entrepreneurship, and business cooperation.
They expressed their interest in working closely with ECCSA to strengthen engagement with Ethiopian businesses and explore mutually beneficial partnerships.
The meeting was also attended by Ms. Neima-Filson Ali, a businesswoman and Vice President of Global Diaspora Djibouti and other representatives of the diaspora community.

