AfCFTA ለኢትዮጵያ የንግድ ዕድሎችን ለማስፋት፣ የኤክስፖርት አቅምን ለማጠናከር እና ከአፍሪካ ገበያዎች ጋር ያለንን ትስስር ለማሳደግ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ለኢትዮጵያ የንግድ ዕድሎችን ለማስፋት፣ የኤክስፖርት አቅምን ለማጠናከር እና ከአፍሪካ ገበያዎች ጋር ያለንን ትስስር ለማሳደግ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።
ሆኖም ፤ የንግድ ዕድል መኖሩ ብቻ በቂ አይደለም፤ ዕድሉን በተግባር ለመጠቀም የገበያ፣ የጉምሩክ፣ የምርት መስፈርት፣ የሰነድ እና ተያያዥ መረጃዎች በቀላሉ ሊገኙና ተደራሽ ሊሆኑ ይገባል። ይህን ማሟላት ካልተቻለ ፤በተለይም ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ለሴቶችና ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች የንግድ ወጪን የሚጨምር ከመሆኑም ባሻገር ጊዜን ሊያባክን የሚችል እንቅፋት ይሆናል።
ስለዚህ ፤ የኢትዮጵያ AfCFTA የሸቀጦች ንግድ መመሪያ (Step-by-Step Guide) እና የንግድ መረጃ ፖርታል (Trade Information Portal) የንግድ ስርዓቶችን ቀላል፣ ግልጽና ተደራሽ በማድረግ የግሉ ዘርፍን ተሳትፎ ለማሳደግ ወሳኝ መሳሪያዎች ናቸው።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት AfCFTA የሚያስገኛቸው ዕድሎች ለኢትዮጵያ ንግዶች ተጨባጭ ውጤት እንዲያመጡ፣ ከተለመደው የሸቀጦች ኤክስፖርት ባሻገር በአህጉራዊ የእሴት ሰንሰለቶች ውስጥ በተወዳዳሪነት የሚሳተፉ የኢትዮጵያ ቢዝነሶችን በማፍራት ረገድ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሁሉ እንደሚወጣ በዚህ አጋጣሚ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
❇️❇️❇️❇️
The African Continental Free Trade Area (AfCFTA) presents a significant opportunity for Ethiopia to expand trade opportunities, strengthen its export capacity, and deepen its integration with African markets.
However, the existence of trade opportunities alone is not enough. To translate these opportunities into practical business outcomes, market information, customs requirements, product standards, documentation, and other relevant information must be easily accessible and understandable. Failure to provide such information can become a major barrier, particularly for micro, small and medium-sized enterprises (MSMEs), women and young entrepreneurs, by increasing the cost of doing business and consuming valuable time.
In this regard, the Ethiopian AfCFTA Step-by-Step Guide for Trading in Goods and the Trade Information Portal are important tools for making trade procedures simpler, clearer and more accessible, while encouraging greater participation by the private sector.
By providing businesses with practical and reliable information, these instruments can help Ethiopian enterprises navigate trade procedures more efficiently and take greater advantage of opportunities available under the AfCFTA.
The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) is committed to fulfilling its responsibility in ensuring that the opportunities created by the AfCFTA translate into tangible results for Ethiopian businesses. This includes supporting enterprises to move beyond traditional commodity exports and become more competitive participants in continental value chains.
Sebsib Abafira Abajobir
President, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

