ዶ/ር ዓይናለም አባይነህ በኢትዮጵያ የስሪላንካ ኤምባሲ ሁለተኛ ጸሐፊ ፑርኒማ አበይጉናሴካራ ጋር ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዓይናለም አባይነህ በኢትዮጵያ የስሪላንካ ኤምባሲ ሁለተኛ ጸሐፊ ፑርኒማ አበይጉናሴካራ ጋር በሁለቱ አገራት የንግድና የኢንቨስትመንት ትብብር ዙሪያ ተወያይተዋል።
ለሁለቱም አገራት የጋራ ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያበረክቱ የትብብር መስኮችን ማስፋት፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ትስስሮችን ማጠናከር እንዲሁም በሁለቱ አገራት የሚገኙ ኩባንያዎች የንግድ ግንኙነት እንዲፈጥሩ ስለሚያስፈልጉ ጉዳዮች ሀሳብ ተለዋውጠዋል።
ሚስ ፑርኒማ አበይጉናሴካራ የስሪላንካ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለይም በማዕድን፣ በመድኃኒት፣ በጨርቃጨርቅና በሌሎች ዘርፎች ላይ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው፤ አንዳንድ የስሪላንካ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ አሁንም እየሠሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ምክትል ፕሬዚደንቱ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለስሪላንካ ኩባንያዎች ምቹ የንግድና የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን አብራርተውላቸዋል፡፡
በሁለቱ አገራት የሚዘጋጁ ኤግዚቢሽኖች፣ የንግድ ትርዒቶችና ትልልቅ የንግድ ዝግጅቶች ኩባንያዎች የገበያ ዕድላቸውን እንዲያሰፉ፣ አዳዲስ የንግድ አጋሮችን እንዲያፈሩና የንግድ ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ ጠቃሚ መድረኮች መሆናቸውን ዶ/ር አይናለም ገልጸዋል።
በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ኩባንያዎች የፊታችን ጥር አጋማሽ በስሪላንካ በሚካሄደው International Sri Lanka Expo 2027 እንዲሳተፉ ግብዣ ቀርቦላቸዋል።
ዶ/ር አይናለም በበኩላቸው የስሪላንካ ኩባንያዎች እኤአ ጥር መጨረሻ በአዲስ አበባ በሚካሄደው 16ኛው ኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት እንዲሳተፉ ግብዣ አቅርበውላቸዋል።

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations Vice President Dr. Aynalem Abayneh,
held a meeting with Ms. Poornima Abeygunasekara, Second Secretary of the Embassy of Sri Lanka in Ethiopia, to discuss opportunities for strengthening economic cooperation between the two countries.
The two sides exchanged views on the trade and investment interests of companies from both countries and discussed ways to strengthen business-to-business cooperation between Ethiopian and Sri Lankan companies.
During the discussion, Ms. Abeygunasekara highlighted the interest of Sri Lankan companies in exploring opportunities in Ethiopia, particularly in mining, pharmaceuticals, textiles, and other sectors. She also noted that a number of Sri Lankan companies are already operating in different industrial parks in Ethiopia, reflecting the existing business ties between the two countries.
The vice President explained that Ethiopia’s growing role as an investment hub in Africa presents opportunities for Sri Lankan companies to expand their trade and investment activities in the country. He also emphasized the importance of exhibitions, trade fairs, and major business events in both countries as important platforms for market expansion, business networking, and strengthening cooperation between the private sectors.
In this regard, Ethiopian companies have been invited to participate in the International Sri Lanka Expo 2027, scheduled to take place in mid-January 2027.
The Vise president also invited Sri Lankan companies to participate in the 16th Ethio-Chamber International Trade Fair, which is scheduled to be held in Addis Ababa in early February 2027.

