Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 09, 2025 .

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ግብይት  የማሥጀመሪያ መርኃ-ግብር  እየተካሄደ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ግብይት  የማሥጀመሪያ መርኃ-ግብር  እየተካሄደ ነው፡፡

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ዋና ጸሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ ተወካይ፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆብርና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የንግዱ ማኀበረሠብ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ግብይቱ ሲጀመር ሥጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና በየብስ ትራንስፖርት ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ አፍሪካ ተልከዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ተግባራዊነት ከአፍሪካ ህብረት ምስረታ ጀምሮ በግንባር ቀደምነት ስትሠራበት የቆየችው ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል።

ሥምምነቱ ለአባል ሀገራቱ የኢኮኖሚ ለውጥ እንዲሁም እድገትና ለውጥ፣ ለገበያ መስፋፋት፣ ህዝቦችን በንግድ የሚያሥተሣሥር እንዲሁም ኢንቨሥትመንት የሚያበረታታ የወጭና ገቢ ንግድን የሚያዘምንና የተሣለጠ የንግድ ሥርዓት መፍጠር የሚያሥችል ነው።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia